መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ሐምሌ 2013

ይህ እትም ኢየሱስ በተናገረው ትንቢት ውስጥ የተጠቀሱት ክንውኖች ፍጻሜያቸውን ከሚያገኙበት ጊዜ ብሎም ከታማኝና ልባም ባሪያ ማንነት ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል የነበረንን መረዳት እንድናስተካክል የሚያደርጉንን በርካታ አዳዲስ ሐሳቦች የያዘ ነው።

“ንገረን፣ እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙት መቼ ነው?”

በማቴዎስ ምዕራፍ 24 እና 25 ላይ በተገለጸው የኢየሱስ ትንቢት ውስጥ የተጠቀሱት ክንውኖች የሚፈጸሙበትን ጊዜ በተመለከተ በነበረን መረዳት ላይ ምን ማስተካከያ ተደርጓል?

“ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ”

ኢየሱስ ስለ ስንዴውና ስለ እንክርዳዱ የተናገረው ምሳሌ ስንዴውና እንክርዳዱ የሚዘሩበት፣ አብረው የሚያድጉበትና የመከር ወቅት እንደሚኖር ይገልጻል። የመከሩን ጊዜ አስመልክቶ በነበረን መረዳት ላይ ምን ዓይነት ማስተካከያ ተደርጓል?

በጥቂቶች ተጠቅሞ ብዙኃኑን መመገብ

ኢየሱስ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ለነበሩት ጉባኤዎች መንፈሳዊ ምግብ ያቀረበው እንዴት ነው? በዛሬው ጊዜስ የሚጠቀምበት መንገድ ከጥንቱ ጋር ተመሳሳይ ነው?

“ታማኝና ልባም ባሪያ በእርግጥ ማን ነው?”

ይህ ርዕስ ስለ ታማኝና ልባም ባሪያ የሚናገረውን ምሳሌ በተረዳንበት መንገድ ላይ ማስተካከያ እንድናደርግ ያስችለናል። መንፈሳዊ ጤንነታችን የተመካው ይህን ባሪያ በማወቃችን ላይ ነው የምንልበትን ምክንያት ከርዕሱ እንድትረዳ እንጋብዝሃለን።

አዲስ የበላይ አካል አባል

ከመስከረም 1, 2012 አንስቶ ወንድም ማርክ ሳንደርሰን የይሖዋ ምሥክሮች በላይ አካል አባል በመሆን ማገልገል ጀምሯል።

የሕይወት ታሪክ

የትም ብንመደብ ጉጉታችን ይሖዋን ማገልገል ነው

በኔዘርላንድ የሚኖሩ አንድ ባልና ሚስት ፈታኝ ሁኔታ ቢያጋጥማቸውም እንዲሁም የአገልግሎት ምድባቸው ቢቀያየርም ሙሉ በሙሉ በይሖዋ መታመን የቻሉት እንዴት እንደሆነ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

“በጣም የሚገርም ሥዕል ነው!”

በጽሑፎቻችን ላይ የሚወጡት ሥዕሎችና ፎቶግራፎች የሚዘጋጁት ስለ ትምህርቱ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖረንና ስሜታችን በጥልቅ እንዲነካ ለማድረግ ታስቦ ነው። ታዲያ ማራኪ ከሆኑት ሥዕሎች ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?