በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የግድያ ሴራ የጠነሰሱት ሰዎች ራሳቸው ተገደሉ!

የግድያ ሴራ የጠነሰሱት ሰዎች ራሳቸው ተገደሉ!

ለወጣት አንባቢያን

የግድያ ሴራ የጠነሰሱት ሰዎች ራሳቸው ተገደሉ!

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳልና በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማት ሞክር። እንዲሁም የባለ ታሪኮቹን ስሜት ለመረዳትና ታሪኮቹ ሕያው እንዲሆኑልህ ለማድረግ ጥረት አድርግ።

ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።ዳንኤል 6:1-28ን አንብብ።

ዳርዮስ ምን ዓይነት ሰው ይመስልሃል? በአእምሮህ የሳልከው እንዴት ዓይነት ቁመና ያለው ሰው አድርገህ ነው? ዳንኤልን እንዴት ባለ የድምፅ ቃና ያነጋገረው ይመስልሃል? (ቁጥር 14, 16 እና 18-20⁠ን ደግመህ አንብብ።)

․․․․․

ዳንኤል የተጣለው በምን ዓይነት ጉድጓድ ውስጥ ነው? የአንበሶቹ ሁኔታስ ምን ይመስል ነበር?

․․․․․

ዳንኤልን የአንበሳ ጉድጓዱ ውስጥ አስገብተው ሲዘጉበት ምን የሆነ ይመስልሃል?

․․․․․

ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ዳርዮስ የሾማቸው የበላይ አስተዳዳሪዎችና መሳፍንቱ በዳንኤል የቀኑት ለምን ነበር? (ቁጥር 3⁠ን ደግመህ አንብብ።)

․․․․․

ዳንኤል ተደብቆ መጸለይ ሲችል ሰው እያየው ለመጸለይ የመረጠው ለምንድን ነው? (ቁጥር 10 እና 11⁠ን ደግመህ አንብብ።)

․․․․․

ዳርዮስ፣ ጸሎትን አስመልክቶ ሕግ እንዲያወጣ የቀረበለት ሐሳብ ጥሩ እንደሆነ የተሰማው ለምን ሊሆን ይችላል? (ቁጥር 7⁠ን ደግመህ አንብብ።)

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ተቃውሞ ሲያጋጥም ደፋር ስለ መሆን።

․․․․․

ስለ ጸሎት አስፈላጊነት።

․․․․․

ይሖዋ ታማኝ አገልጋዮቹን የሚጠብቅ ስለመሆኑ።

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው የትኛው ሁኔታ ነው? ለምንስ?

․․․․․