በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከመጥፎ ጓደኛ ራቅ!

ከመጥፎ ጓደኛ ራቅ!

ለታዳጊ ወጣቶች

ከመጥፎ ጓደኛ ራቅ!

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

ዋነኞቹ ባለ ታሪኮች፦ ዲና፣ ሴኬም፣ ያዕቆብ፣ ስምዖንና ሌዊ

ታሪኩ በአጭሩ፦ ሴኬም ዲናን በፆታ አስነወራት፤ ከዚያም በሁኔታው የተናደዱት ወንድሞቿ የበቀል እርምጃ ወሰዱ።

1 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።​ዘፍጥረት 34:1-31ን አንብብ።

ዲና በከነዓን ካሉት ጓደኞቿ ጋር ስትገናኝ ምን ታደርግ የነበረ ይመስልሃል?

․․․․․

ሴኬም ዲናን ‘በጣፈጠ አንደበት ለማናገር’ ምን ዘዴ የተጠቀመ ይመስልሃል?

․․․․․

በቁጥር 30 ላይ በተገለጸው መሠረት ያዕቆብ፣ ስምዖንንና ሌዊን ሲቆጣቸው በአነጋገሩ ላይ ምን ዓይነት ስሜት ሲንጸባረቅ ይታይሃል?

․․․․․

2 ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ዲና ከከነዓን ሴቶች ጋር ጊዜ ለማሳለፍ ሁልጊዜ ትሄድ የነበረው ለምን ይመስልሃል? (ለምሳሌ ያህል፣ እሷም ሆነች እነሱ የሚወዱት አብረው ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር ምን ሊሆን ይችላል? ቤቷ ስትሆን የማታገኘው ከነዓናውያን ጋ ስትሄድ ግን የምታገኘው ነገር ምን ሊሆን ይችላል?)

․․․․․

ዲና፣ ሴኬም ምን ጥሩ ጥሩ ባሕርያት እንዳሉት ተመልክታ ሊሆን ይችላል? (ቁጥር 3, 12, 19ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

መጽሐፍ ቅዱስ ዲና ከሴኬም ጋር የፆታ ግንኙነት መፈጸም እንዳልፈለገች የሚጠቁመው እንዴት ነው? (ቁጥር 2⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

ስምዖንና ሌዊ በሴኬም ከተማ የሚኖሩትን ወንዶች በመግደል መበቀላቸው ትክክል ይመስልሃል? ከሆነ ለምን? ካልሆነስ ለምን?

․․․․․

3 ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ጓደኞችህን በጥበብ ስለ መምረጥ።

․․․․․

የእውነት የሚያናድድ ነገር ቢያጋጥምህም እንኳ ራስን ስለ መቆጣጠር።

․․․․․

ልትሠራበት የሚገባ ተጨማሪ ነገር።

ለአምላክ የሥነ ምግባር ደንቦች ምንም ግድ የሌላቸው ሰዎች አባብለው የፆታ ብልግና እንድትፈጽም እንዳያደርጉህ ምን ማድረግ ትችላለህ?

․․․․․

4 ከዚህ ታሪክ ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው ምንድን ነው? ለምንስ?

․․․․․

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎች ለማግኘት የይሖዋ ምሥክሮችን ጠይቅ ወይም www.watchtower.org ተመልከት።