መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 2013 | አምላክ ጨካኝ ነው?
በዛሬው ጊዜ የምናያቸው የተፈጥሮ አደጋዎችና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጹት መለኮታዊ የጥፋት ፍርዶች አንዳንድ ሰዎች አምላክ ጨካኝ ነው ብለው እንዲያስቡ አድርገዋቸዋል። ታዲያ እውነታዎቹን ስንመረምር ምን መደምደሚያ ላይ እንደርስ ይሆን?
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
ሰዎች አምላክ ጨካኝ ነው የሚሉት ለምንድን ነው?
ብዙ ሰዎች አምላክ ጨካኝ እንደሆነ ወይም ለሰዎች ምንም ግድ እንደሌለው ይሰማቸዋል። ይህን ጉዳይ በሚመለከት መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
የተፈጥሮ አደጋዎች አምላክ ጨካኝ እንደሆነ ያረጋግጣሉ?
እውነተኛው አምላክ ጭካኔን እንደሚጠላ ይታወቃል፤ ታዲያ የተፈጥሮ አደጋዎች የንጹሐን ሰዎችን ሕይወት እንዲቀጥፉ የፈቀደው ለምንድን ነው?
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
መለኮታዊ የጥፋት ፍርዶች—አምላክ ጨካኝ እንደሆነ ያሳያሉ?
ይህን ጥያቄ ለመመለስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጹ ሁለት መለኮታዊ የጥፋት ፍርዶችን ተመልከት—በኖኅ ዘመን የደረሰው የጥፋት ውኃ እና ከነዓናውያንን ለማጥፋት የተወሰደው እርምጃ።
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
በአምላክ ላይ እምነት መጣል ትችላለህ?
አምላክ እምነት ልትጥልበት የምትችል ጓደኛህ ሊሆን እንደሚችል ማወቅህ ምን ያህል እርካታ እንደሚያስገኝልህ ለመረዳት ይህን ርዕስ አንብብ።
መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል
“ቄስ የመሆን ፍላጎት ነበረኝ”
ሮቤርቶ ፓቼኮ በልጅነቱ የካቶሊክ ቄስ የመሆን ፍላጎት ነበረው። ሕይወቱ እንዲለወጥ ያደረገው ምን እንደሆነ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።
ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?
የእንጀራ ልጆች ባሉበት ቤተሰብ ውስጥ ከሌሎች ጋር ጥሩ ግንኙነት መመሥረት
የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች የእንጀራ ወላጆች ከጓደኞች፣ ከዘመዶች ሌላው ቀርቶ ከባለቤታቸው የቀድሞ የትዳር ጓደኛ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖራቸው የሚረዷቸው እንዴት ነው?
ወደ አምላክ ቅረብ
አምላክ በእርግጥ ስለ አንተ ያስባል?
አምላክ በግለሰብ ደረጃ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚመለከትህ እና እንደሚያስብልህ ማመን ይከብድሃል? ኢየሱስ በዮሐንስ 6:44 ላይ የተናገረው ሐሳብ አምላክ ለአገልጋዮቹ በግለሰብ ደረጃ እንደሚያስብላቸው ጠንካራ ማስረጃ ይሰጠናል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
አምላክ ከባድ ኃጢአቶችን ይቅር ይላል? የአምላክን ሞገስ ለማግኘት ምን ማድረግ ይኖርብናል?
እውነት
የት ሊገኝ ይችላል? ለእርስዎና ለቤተሰብዎ ምን ጥቅም ያስገኛል? የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት የይሖዋ ምሥክሮች በሚያዘጋጁት የሦስት ቀን የአውራጃ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ በአክብሮት እንጋብዝዎታለን።
በተጨማሪም . . .
የይሖዋ ምሥክሮች የሚድኑት እነሱ ብቻ እንደሆኑ ይሰማቸዋል?
መጽሐፍ ቅዱስ የመዳን አጋጣሚ የተከፈተው ለእነማን እንደሆነ ይናገራል።