በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ክርስቶስ ተመልሶ የሚመጣበት ዓላማ ምንድን ነው?

ኢየሱስ በ33 ዓ.ም. ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት፣ ተመልሶ እንደሚመጣ ቃል ገብቷል። ኢየሱስ፣ ለረጅም ጊዜ ወደ ሩቅ አገር ከሄደ በኋላ ንጉሣዊ ሥልጣኑን ተረክቦ ከሚመለስ አንድ መስፍን ጋር ራሱን አመሳስሏል። ኢየሱስ ተመልሶ የሚመጣበት ዓላማ ለሰው ልጆች መልካም አስተዳደር ለማስፈን ነው።—ሉቃስ 19:11, 12ን አንብብ።

ኢየሱስ ለሰው ዘሮች መልካም አስተዳደር ያመጣላቸዋል

ክርስቶስ የሚመለሰው በምን ዓይነት አካል ነው? ከሙታን የተነሳው የማይታይ መንፈሳዊ አካል ሆኖ ነው። (1 ጴጥሮስ 3:18) ከዚያም ወደ ሰማይ ሄዶ በአምላክ ቀኝ ተቀመጠ። (መዝሙር 110:1) በጣም ቆይቶ ደግሞ “ጥንታዌ ጥንቱ” በሆነው በይሖዋ አምላክ ፊት የቀረበ ሲሆን እሱም በሰው ልጆች ላይ የመግዛት ሥልጣን ሰጠው። ስለዚህ ኢየሱስ የሚመለሰው ሰው ሆኖ ሳይሆን በዓይን የማይታይ ንጉሥ ሆኖ ነው።—ዳንኤል 7:13, 14ን አንብብ።

ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ ምን ያደርጋል?

ኢየሱስ በዓይን በማይታይ ሁኔታ ከመላእክቱ ጋር ተመልሶ ሲመጣ በሰው ዘሮች ላይ ይፈርዳል። ክፉ ሰዎችን የሚያጠፋ ሲሆን እሱን እንደ ንጉሣቸው አድርገው ለተቀበሉት ግን ዘላለማዊ ሕይወት ይሰጣቸዋል።—ማቴዎስ 25:31-33, 46ን አንብብ።

ኢየሱስ ንጉሥ ሆኖ ሲገዛ ምድርን ወደ ገነትነት ይለውጣታል። እንዲሁም ሙታንን በማስነሳት ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ተደስተው እንዲኖሩ ያደርጋል።—ሉቃስ 23:42, 43ን አንብብ።