ልቤን እጠብቃለሁ
አውርድ፦
1. መልካም ማድረግ ነው ምኞቴ፣
ቢታገልም ከብዶት ውስጤ።
‘ከንቱ ነሽ’ ብሎ ልቤ፣
ይከሰኛል ሐሳቤ።
አምላኬ ሆይ፣ ስማኝ ’ባክህ፤
ጭንቀቴ በዝቷል፣ ውስጤን ልንገርህ።
ክፉው ልቤ ሳይረታኝ
ቀና አድርገኝ፤ ልበርታ።
(አዝማች)
ልጠብቅ ልቤን፤ ልግራው ሐሳቤን።
በጎ፣ በጎ ላስብ ሁሌ።
ለምን ብዬ ልጣ ሰላሜን!
ለክፉ ሐሳብ አልከፍትም በሬን።
2. የኔስ ጠላት ይህ ልቤ ነው፣
መጠራጠር የሚቀናው።
ፍቅርህን ማመን ከብዶት፣
ሊተክዝ ጀመር ደግሞ።
ስወጣ ግን ለማገልገል፣
ብርቱ ነኝ ያኔ ቃሉን ስናገር።
በቅቶኛል ስል ደክሜ፤
ደግፈህ ያዝከኝ፣ አምላኬ።
(አዝማች)
ልቤን፣ ሐሳቤን እጠብቃለሁ።
በጎ፣ በጎ አስባለሁ።
ለምን ብዬ ልጣ ሰላሜን!
ለክፉ ሐሳብ አልከፍትም በሬን።
አልከፍትም በሬን።
(መሸጋገሪያ)
እጅ አልሰጥም፤ እዋጋለሁ።
ለልቤ ዘብ እቆማለሁ።
አልተክዝም፣ አልጨነቅም፤
ይሖዋ፣ አንተስ ትተኸኝ አታውቅም።
ትተኸኝ አታውቅም።
(አዝማች)
ልቤን፣ ሐሳቤን እጠብቃለሁ።
በጎ፣ በጎ አስባለሁ።
ለምን ብዬ ልጣ ሰላሜን!
ለክፉ ሐሳብ አልከፍትም በሬን።