የሰላም ሰው
አውርድ፦
1. ጀምበሯ ሳትከር፣ ገና ማለዳ፣ ሰው ሁሉ ሆደ ባሻ፤
ቀንበር ሆነ፣ ኑሮ ጨከነ፣ ብሶተኛው በዛ።
እኔው ልታገሥ፣ ቃሉ ’ንዳለው ‘አትቸኩል ለቁጣ’፤
ልተወው ንቄ፣ ላፍታ ጸልዬ፣ ለምን ሰላሜን ልጣ?
(አዝማች)
ባበደው ዓለም፣ በሚታመሰው፣ ትግል ነው ለሰላም ሰው።
መቻል ግን አለው ፍሬ፣ ቢከብድም ዛሬ፤ ነገማ አዲስ ዓለም ነው።
2. በ’ለት ውሎዬ፣ ደፋ ስል ቀና፣ ከሰው ባልደርስም ገና፤
በትንሹ፣ በትልቁ፣ ቱግ የሚል መች ጠፋና።
ቃሉ ቢሻክር፣ ዘልፎም ቢናገር፣ ማን አየው ሕመሙን?
ሆድ ለባሰው ሰው፣ ኑሮ መች አነሰው፤ አልጨምርም በቁስሉ።
(አዝማች)
ባበደው ዓለም፣ በሚታመሰው፣ ትግል ነው ለሰላም ሰው።
መቻል ግን አለው ፍሬ፣ ቢከብድም ዛሬ፤ ነገማ አዲስ ዓለም ነው።
(መሸጋገሪያ)
ክፉን በመልካም መርታት፣
ዳገት አይደል ሽቅብ መውጣት?
ልቤ ግን ረግቷል፤ አደብ ገዝቷል፤
ባምላክ ሰላም ተረጋግቷል።
3. ሳምንቱ አልቆ፣ ቅዳሜ ደርሶ፣ ወጣን ቅን ልብ ፍለጋ፤
ሰሚ ጆሮ ’ንዳለ፣ ’ማይሰማም አለ፣ አልፎም ጠብ የሚጠራ።
ካልጣመው ይቅር፣ ነገር ከሚከር፣ ይሻላል እልፍ ሲሉ፤
ያለማገዶ እሳት መች ነዶ፤ አይጠቅምም መቆስቆሱ።
(አዝማች)
ባበደው ዓለም፣ በሚታመሰው፣ ትግል ነው ለሰላም ሰው።
መቻል ግን አለው ፍሬ፣ ቢከብድም ዛሬ፤ ነገማ አዲስ ዓለም ነው።
(አዝማች)
ባበደው ዓለም፣ በሚታመሰው፣ ትግል ነው ለሰላም ሰው።
መቻል ግን አለው ፍሬ፣ ቢከብድም ዛሬ፤ ነገማ አዲስ ዓለም ነው።