በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም

የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም

መጽሐፍ ቅዱስ ለሕይወታችን የሚጠቅም ከሁሉ የላቀ ጥበብ ያዘለ መመሪያ ይዟል። መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ የምታነብ፣ ባነበብከው ላይ ዘወትር የምታሰላስል እንዲሁም የተማርከውን በሥራ ላይ የምታውል ከሆነ “መንገድህ ይቃናልሃል።” (ኢያሱ 1:8፤ መዝሙር 1:1-3) በተጨማሪም አምላክንና ልጁን ኢየሱስን ማወቅ ትችላለህ፤ እንዲህ ያለው እውቀት ደግሞ መዳን ያስገኝልሃል።—ዮሐንስ 17:3

ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስን በምን ዓይነት ቅደም ተከተል ማንበብ ትችላለህ? የተለያዩ አማራጮች አሉህ። ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍቱን አሁን ባሉበት ቅደም ተከተል አሊያም በተለያዩ ርዕሶች ከፋፍለህ ለማንበብ ይረዳሃል። ለምሳሌ፣ አምላክ ከጥንት እስራኤላውያን ጋር ስለነበረው ግንኙነት የሚገልጸውን ታሪክ ለማወቅ የተወሰኑ ክፍሎችን መርጠህ ማንበብ ትችላለህ። ወይም ደግሞ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ስለነበረው የክርስቲያን ጉባኤ አጀማመርና እድገት የሚተርኩ ዘገባዎችን ለማግኘት ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ማንበብ ትችላለህ። በፕሮግራሙ መሠረት የተወሰኑ ምዕራፎችን በየዕለቱ ካነበብክ ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ዓመት ውስጥ አንብበህ መጨረስ ትችላለህ።

ለየዕለቱም ይሁን ለአንድ ዓመት የሚሆን አሊያም ለጀማሪዎች የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም የምትፈልግ ከሆነ ይህ ፕሮግራም ይጠቅምሃል። ይህን የሚታተም የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም ካወረድክ በኋላ ዛሬ ነገ ሳትል ማንበብ ጀምር።