ክርስቲያናዊ ሕይወት
በይሖዋ እንደምንታመን የምናሳይባቸው ሦስት መንገዶች
ዳዊት ጎልያድን ማሸነፍ የቻለው በይሖዋ ስለታመነ ነው። (1ሳሙ 17:45) ይሖዋ ለሁሉም አገልጋዮቹ ብርታቱን ማሳየት ይፈልጋል። (2ዜና 16:9) በራሳችን ተሞክሮና ችሎታ ሳይሆን ይሖዋ በሚሰጠው እርዳታ እንደምንታመን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? እስቲ ሦስት መንገዶችን እንመልከት፦
-
አዘውትራችሁ ጸልዩ። ስህተት ከሠራችሁ በኋላ ይቅርታ ለመጠየቅ ብቻ ሳይሆን ስህተት ለመሥራት የሚፈትን ሁኔታ ሲያጋጥማችሁ ብርታት ለማግኘትም ጸልዩ። (ማቴ 6:12, 13) ይሖዋ አስቀድማችሁ የወሰናችሁትን ነገር እንዲባርክላችሁ ከመለመን ይልቅ ውሳኔ ከማድረጋችሁ በፊት መመሪያና ጥበብ እንዲሰጣችሁ ጸልዩ።—ያዕ 1:5
-
መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብና የማጥናት ልማድ ይኑራችሁ። መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ አንብቡ። (መዝ 1:2) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጠቀሱ ሰዎች ታሪክ ላይ አሰላስሉ፤ እንዲሁም ያገኛችሁትን ትምህርት ተግባራዊ አድርጉ። (ያዕ 1:23-25) ከስብከቱ ሥራ ጋር በተያያዘ በራሳችሁ ተሞክሮ ከመመካት ይልቅ አገልግሎት ከመውጣታችሁ በፊት ተዘጋጁ። ለጉባኤ ስብሰባዎች አስቀድማችሁ በመዘጋጀት ከስብሰባዎቹ ሙሉ ጥቅም አግኙ
-
ከይሖዋ ድርጅት ጋር ተባብራችሁ ሥሩ። ድርጅቱ ካወጣቸው ወቅታዊ መመሪያዎች ጋር በሚገባ ተዋወቁ፤ እንዲሁም መመሪያዎቹን ዛሬ ነገ ሳትሉ ተግባራዊ አድርጉ። (ዘኁ 9:17) ሽማግሌዎች የሚሰጡትን ምክርና መመሪያ አዳምጡ።—ዕብ 13:17
ስደትን የምንፈራበት ምንም ምክንያት የለም የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
• በቪዲዮው ላይ የታዩት ወንድሞችና እህቶች ምን ነገሮች አስፈርተዋቸው ነበር?
• ፍርሃታቸውን እንዲያሸንፉ የረዳቸው ምንድን ነው?