ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
በስሜታዊነት እርምጃ ትወስዳላችሁ?
ዳዊት ምክንያታዊ ጥያቄ ቢያቀርብም ከናባል ያገኘው ምላሽ ስድብ ነበር (1ሳሙ 25:7-11፤ ia 78 አን. 10-12)
ዳዊት ስሜታዊ በመሆን በናባል ቤት ውስጥ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ለመግደል ወሰነ (1ሳሙ 25:13, 21, 22)
አቢጋኤል ዳዊትን የደም ባለ ዕዳ ከመሆን ጠብቃዋለች (1ሳሙ 25:25, 26, 32, 33፤ ia 80 አን. 18)
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘በምበሳጭበት ወይም ተስፋ በምቆርጥበት ጊዜ ስሜታዊ መሆን ይቀናኛል? ዕቃ በምገዛበት ጊዜስ በስሜት እነዳለሁ? ወይስ እርምጃ ከመውሰዴ በፊት ቆም ብዬ ውጤቱን አመዛዝናለሁ?’—ምሳሌ 15:28፤ 22:3