በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—መጽሔት ለማበርከት የራስህን መግቢያ አዘጋጅ
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በስብሰባው አስተዋጽኦ ላይ የሚገኙት የአቀራረብ ናሙናዎች ጠቃሚ እንደሆኑ ባይካድም የሚያገለግሉት እንደ መነሻ ሐሳብ ብቻ ነው። በራስህ አባባል መናገር ያስፈልግሃል። የራስህን አቀራረብ መጠቀም ትፈልግ ይሆናል፤ ወይም በአካባቢህ ያሉ ሰዎችን ትኩረት ይበልጥ የሚስበው ሌላ ርዕስ እንደሆነ ሊሰማህ ይችላል። ከሆነ መጽሔቱን ካነበብክ፣ የአቀራረብ ናሙናዎቹንና በቪዲዮ የሚቀርቡትን ሠርቶ ማሳያዎች ከተመለከትክ በኋላ የራስህን መግቢያ ለማዘጋጀት የሚከተሉትን ሐሳቦች መጠቀም ትችላለህ።
ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
ራስህን እንዲህ በማለት ጠይቅ፦ ‘ከአቀራረብ ናሙናዎቹ መካከል አንዱን መጠቀም እችላለሁ?’
አዎ
-
መጀመሪያ የምትናገረውን ነገር አዘጋጅ። በአካባቢው የተለመደውን ሰላምታ ከሰጠህ በኋላ የመጣህበትን ምክንያት አጠር አድርገህ ተናገር። (ለምሳሌ፦ “የመጣሁት . . . ”)
-
ከጥያቄው ወደ ጥቅሱ ወይም ለማበርከት ወደምትናገረው ሐሳብ ለመሸጋገር የምትጠቀምባቸውን ሐሳቦች አዘጋጅ። (ለምሳሌ፦ አንድን ጥቅስ ለማስተዋወቅ እንዲህ ማለት ትችላለህ፦ “ለዚህ ጥያቄ የሚሆን አጥጋቢ መልስ በዚህ ጥቅስ ላይ ይገኛል።”)
አይ
-
በክልልህ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ትኩረት ሊስብ እንደሚችል የሚሰማህን አንድ ርዕስ ከመጽሔቱ ላይ ምረጥ
-
የቤቱን ባለቤት ትኩረት የሚስብና ውይይት ለመጀመር የሚያስችል የአመለካከት ጥያቄ አዘጋጅ፤ ጥያቄው ግን የቤቱን ባለቤት የሚያፋጥጥ እንዳይሆን ተጠንቀቅ። (ለምሳሌ፦ በመጽሔቱ ገጽ 2 ላይ የሚገኙትን ጥያቄዎች መጠቀም ይቻላል።)
-
የምታነብበውን ጥቅስ ምረጥ። (የምታበረክተው ንቁ! ከሆነ ጥቅስ ማንበብ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል፤ ምክንያቱም ይህ መጽሔት የሚዘጋጀው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ብዙም እውቀት ለሌላቸው ወይም በሃይማኖት ላይ እምነት ላጡ ሰዎች ነው።)
-
የቤቱ ባለቤት ይህን ርዕስ ማንበቡ የሚጠቅመው እንዴት እንደሆነ የሚገልጽ አንድ ወይም ሁለት ዓረፍተ ነገር አዘጋጅ
መልስህ ምንም ይሁን ምን
-
በተመላልሶ መጠይቅ ወቅት የምትወያዩበት ጥያቄ አዘጋጅ
-
በዝግጅት ወቅት ተመላልሶ ለማድረግ ስትመጣ የምትናገራቸውን ነገሮች ለማስታወስ የሚረዳህ ማስታወሻ ያዝ