ክርስቲያናዊ ሕይወት
የላቀ ቦታ የምሰጠው ነገር ምንድን ነው?
ያዕቆብ የላቀ ቦታ የሚሰጠውን ነገር ማለትም የይሖዋን በረከት ለማግኘት ሲል ከአንድ መልአክ ጋር ታግሏል። (ዘፍ 32:24-31፤ ሆሴዕ 12:3, 4) እኛስ? ይሖዋን ለመታዘዝና የእሱን በረከት ለማግኘት የቻልነውን ሁሉ እያደረግን ነው? ለምሳሌ፣ በጉባኤ ስብሰባ ላይ ከመገኘትና ትርፍ ሰዓት ከመሥራት አንዱን መምረጥ ቢኖርብን የቱን እንመርጣለን? ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንን እና ጥሪታችንን ሳንሰስት ለይሖዋ የምንሰጥ ከሆነ እሱ ደግሞ ‘ማስቀመጫ እስክናጣ ድረስ የተትረፈረፈ በረከት ያፈስልናል።’ (ሚል 3:10) ይሖዋ ይመራናል፤ ይጠብቀናል፤ እንዲሁም የሚያስፈልገንን ነገር ያሟላልናል።—ማቴ 6:33፤ ዕብ 13:5
በመንፈሳዊ ግቦች ላይ ማተኮራችሁን ቀጥሉ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
እህት፣ የምትወደው ነገር ፈተና የሆነባት እንዴት ነው?
-
ሰብዓዊ ሥራችን ፈተና ሊሆንብን የሚችለው እንዴት ነው?
-
ጢሞቴዎስ በመንፈሳዊ የጎለመሰ ክርስቲያን ሆኖ ሳለ አዳዲስ ግቦች ማውጣት ያስፈለገው ለምንድን ነው?—1ጢሞ 4:16
-
ዋናው ሥራችን ምን እንደሆነ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?