ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ይሖዋ ምድሪቱን ያከፋፈለበት ጥበብ የሚንጸባረቅበት መንገድ
ይሖዋ ዕጣ በማውጣት መመሪያ ሰጠ፤ ዕጣው፣ እያንዳንዱ ነገድ የት አካባቢ እንደሚሰፍር የሚጠቁም ሳይሆን አይቀርም (ኢያሱ 18:10፤ it-1 359 አን. 1)
ይሖዋ፣ ያዕቆብ ሊሞት ሲል የተናገረው ትንቢት ፍጻሜውን እንዲያገኝ አድርጓል (ኢያሱ 19:1፤ it-1 1200 አን. 1)
ይሖዋ፣ የእያንዳንዱን ነገድ ርስት ስፋት ሕዝቡ ራሱ እንዲወስን አደረገ (ኢያሱ 19:9፤ it-1 359 አን. 2)
ምድሪቱ የተከፋፈለችው፣ በነገዶቹ መካከል ቅናት ወይም ጥል እንዳይኖር በሚያደርግ መንገድ ነው። ይህ ታሪክ ይሖዋ በአዲሱ ዓለም ውስጥ ነገሮችን ስለሚመራበት መንገድ ምን እምነት እንዲያድርብህ ያደርጋል?