ከኅዳር 15-21
ኢያሱ 23–24
መዝሙር 50 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ኢያሱ ለብሔሩ የሰጠው የመጨረሻ ማሳሰቢያ”፦ (10 ደቂቃ)
መንፈሳዊ ዕንቁዎች፦ (10 ደቂቃ)
ኢያሱ 24:2—የአብርሃም አባት ታራ ጣዖት አምላኪ ነበር? (w04 12/1 12 አን. 1)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ይሖዋን፣ የመስክ አገልግሎትን ወይም ሌሎች ነገሮችን በተመለከተ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ) ኢያሱ 24:19-33 (th ጥናት 11)
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
መመሥከር፦ (3 ደቂቃ) በውይይት ናሙናው ጀምር። በክልላችሁ ለተለመደ የተቃውሞ ሐሳብ ምላሽ ስጥ። (th ጥናት 2)
ተመላልሶ መጠየቅ፦ (4 ደቂቃ) በውይይት ናሙናው ጀምር። ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን ብሮሹር አበርክት። (th ጥናት 20)
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (5 ደቂቃ) lffi ምዕራፍ 01 ማጠቃለያ፣ ክለሳ እና ግብ (th ጥናት 3)
ክርስቲያናዊ ሕይወት
በሥራ ቦታ ከመጥፎ ጓደኝነት ራቁ፦ (7 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ታማኝነትን የሚሸረሽሩ ነገሮችን አስወግዱ—መጥፎ ጓደኝነት የተባለውን አጭር ድራማ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ መጥፎ ጓደኝነት በእህት ላይ ምን አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሮ ነበር? ምን ማስተካከያ አደረገች? ይህስ የረዳት እንዴት ነው? ከመጥፎ ጓደኝነት መራቅን በተመለከተ ከዚህ አጭር ድራማ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ባላሰብነው ቦታ ጓደኞች ማግኘት፦ (8 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ቪዲዮውን አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ አኪል በትምህርት ቤት ከመጥፎ ጓደኞች ጋር እንዲገጥም ምክንያት የሆነው ነገር ምንድን ነው? ጉባኤ ውስጥ ጥሩ ጓደኞች ያገኘው እንዴት ነው? ይህ አጭር ድራማ፣ ጥሩ ጓደኞች ማግኘት ስለምትችሉበት መንገድ ምን አስተምሯችኋል?
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) rr ምዕ. 16 አን. 1-8፣ ማስተዋወቂያ ቪዲዮ
የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 39 እና ጸሎት