በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ
በጸሎት አማካኝነት የይሖዋን እርዳታ ተቀበሉ
በአንድ ሰው ልብ ውስጥ የእውነት ዘር ሥር እንዲሰድና እንዲያድግ የሚያደርገው ይሖዋ ነው። (1ቆሮ 3:6-9) ስለዚህ በአገልግሎታችን ውጤታማ መሆን የምንችለው ይሖዋ እኛንም ሆነ ጥናቶቻችንን እንዲረዳን ከጠየቅን ብቻ ነው።
ጥናቶቻችሁ የሚደርስባቸውን ተጽዕኖ እንዲቋቋሙና የሚያጋጥሟቸውን መሰናክሎች ማለፍ እንዲችሉ ይሖዋ እንዲረዳቸው ጠይቁ። (ፊልጵ 1:9, 10) ስትጸልዩ፣ የምትፈልጉትን ነገር ለይታችሁ ጥቀሱ። መንፈስ ቅዱስ አስተሳሰባችሁንና ድርጊታችሁን እንዲመራላችሁ ጸልዩ። (ሉቃስ 11:13) ጥናቶቻችሁን እንዴት እንደሚጸልዩ አስተምሯቸው፤ እንዲሁም እንዲጸልዩ አበረታቷቸው። በግላችሁም ሆነ አብራችኋቸው ስትጸልዩ ስማቸውን እየጠራችሁ ጸልዩ።
ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—የይሖዋን እርዳታ ተቀበሉ—ጸሎት የተባለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
ኒታ ጄድን ስታስጠና ምን ተፈታታኝ ነገር አጋጠማት?
-
አንደኛ ቆሮንቶስ 3:6 ኒታን የረዳት እንዴት ነው?
-
ኒታ ያጋጠማት ተፈታታኝ ሁኔታ መፍትሔ ያገኘው እንዴት ነው?