በኢንዶኔዥያ የሚኖሩ እህቶች አምላክን ስማ የተባለውን ብሮሹር ተጠቅመው ሲሰብኩ

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ የካቲት 2016

የአቀራረብ ናሙናዎች

ንቁ! እና አምላክን ስማ የተባለውን ብሮሹር ለማበርከት የሚረዱ ሐሳቦች። ናሙናዎቹን ተጠቅመህ የራስህን የመግቢያ አዘጋጅ።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ነህምያ እውነተኛውን አምልኮ ይወድ ነበር

ነህምያ የኢየሩሳሌምን ግንቦች እንደገና ለመገንባትና እውነተኛውን አምልኮ ለማስፋፋት ያሳየውን ትጋት በዓይነ ሕሊናህ ተመልከት። (ነህምያ 1-4)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ነህምያ የተዋጣለት የበላይ ተመልካች ነበር

ነህምያ ሕዝቡ በእውነተኛው አምልኮ እንዲደሰቱ ረድቷቸዋል። ሥዕሉን በመጠቀም፣ በ455 ዓ.ዓ. በቲሽሪ ወር በኢየሩሳሌም የተከናወኑትን ነገሮች በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል ሞክር። (ነህምያ 8:1-18)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ታማኝ አገልጋዮች ቲኦክራሲያዊ ዝግጅቶችን ይደግፋሉ

በነህምያ ዘመን የነበሩ የይሖዋ ሕዝቦች በተለያዩ መንገዶች እውነተኛውን አምልኮ በፈቃደኝነት ደግፈዋል። (ነህምያ 9-11)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ከሁሉ የተሻለው ሕይወት

በይሖዋ ድርጅት ውስጥ ያሉ ወጣቶች ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ደስታና እርካታ የሚያስገኙ በርካታ አጋጣሚዎች አሉ። በቪዲዮው ላይ ለመወያየት እነዚህን ጥያቄዎች ተጠቀም።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ከነህምያ መጽሐፍ የምናገኘው ጠቃሚ ትምህርት

ነህምያ ለእውነተኛው አምልኮ ጥብቅና ለመቆም በድፍረት የወሰዳቸውን እርምጃዎች በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል ሞክር። (ነህምያ 12-13)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ክልላችሁ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ሁሉ በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ ጋብዙ!

በ2016 የሚከበረው መታሰቢያ በዓል መጋበዣ ወረቀት ለማሰራጨት የምንጠቀምበት የአቀራረብ ናሙና። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ተከታትላችሁ እርዱ።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

አስቴር ለአምላክ ሕዝቦች ጥብቅና ቆማለች

አስቴር ለአምላክ ሕዝቦች ጥብቅና ለመቆም ስትል በድፍረት የወሰደችውን እርምጃ በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል ሞክር። (አስቴር 1-5)