የአቀራረብ ናሙናዎች
ንቁ!
ጥያቄ፦ የመጣሁት በቅርቡ የወጣውን የንቁ! መጽሔት ልሰጥዎት ነው። በገጽ 2 ላይ የሚገኘውን ይህን ጥያቄ ልብ ይበሉ። እርስዎስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ?
ጥቅስ፦ ምሳሌ 24:10
አበርክት፦ ይህ ርዕስ ከዚህ ሐሳብ ጋር የሚስማሙ ሌሎች መመሪያዎችንም ያብራራል።
ንቁ!
ጥያቄ፦ ጓደኛ የምናደርጋቸውን ሰዎች በጥንቃቄ መምረጣችን አስፈላጊ ነው ቢባል አይስማሙም?
ጥቅስ፦ ምሳሌ 13:20
አበርክት፦ ይህ ንቁ! መጽሔት ጥሩ ጓደኛ ለመምረጥ የሚረዱ አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦችን ይዟል። [በገጽ 10 እና 11 ላይ የሚገኙትን ነጥቦች አጉላ።]
አምላክን ስማ
ጥያቄ፦ እንዲህ በመሰለ ዓለም ውስጥ የመኖር አጋጣሚ ቢያገኙ ደስ አይልዎትም? [ገጽ 2 እና 3ን አሳየውና መልስ እንዲሰጥ ዕድል ስጠው።]
ጥቅስ፦ ኤር 29:11
አበርክት፦ ይህ ብሮሹር አምላክን መስማት የምንችለው እንዴት እንደሆነና ለእኛ ያሰበልንን መልካም ነገሮች እንዴት ማግኘት እንደምንችል ያብራራል። [በገጽ 4 እና 5 ላይ ተወያዩ።]
የራስህን መግቢያ አዘጋጅ
ከላይ የተጠቀሱትን ምሳሌዎች እንደ ናሙና አድርገህ በመጠቀም በመስክ አገልግሎት ላይ የምትጠቀምበት የራስህን አቀራረብ አዘጋጅ።