በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁን ከመጥፎ ጓደኝነት እንዲርቁ እርዷቸው
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ከይሖዋ ጋር ወዳጆች መሆን ከፈለጉ ጥሩ የጓደኛ ምርጫ ማድረግ ይኖርባቸዋል። (መዝ 15:1, 4) ጥሩ ጓደኞች ትክክለኛውን ነገር እንዲያደርጉ በጎ ተጽዕኖ ያሳድሩባቸዋል።—ምሳሌ 13:20፤ lff ምዕራፍ 48
ጥናቶቻችሁ ከመጥፎ ጓደኝነት እንዲርቁ ስትረዱ ራሳችሁን በእነሱ ቦታ ለማስቀመጥ ጥረት አድርጉ። በዓለም ካሉ ጓደኞቻቸው መላቀቅ ሊከብዳቸው ይችላል። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ ከምታጠኑበት ፕሮግራም ውጭም ትኩረት እንደምትሰጧቸው አሳዩአቸው። ለምሳሌ የጽሑፍ መልእክት ልትልኩላቸው፣ ስልክ ልትደውሉላቸው ወይም ጎራ ብላችሁ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ጥናቶቻችሁ እድገት እያደረጉ ሲሄዱ ደግሞ ከሌሎች ወንድሞችና እህቶች ጋር ጊዜ ስታሳልፉ እነሱንም ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። ይህም ካጡት ነገር ይልቅ የሚያገኙት ነገር እጅግ እንደሚበልጥ እንዲያስተውሉ ያደርጋቸዋል። (ማር 10:29, 30) እናንተም የይሖዋ ቤተሰብ በቁጥር ሲያድግ ስታዩ ትደሰታላችሁ።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁን ከመጥፎ ጓደኝነት እንዲርቁ እርዷቸው የሚለውን አጭር ድራማ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
መጥፎ ጓደኝነት ምንድን ነው?—1ቆሮ 15:33
-
ጄድ የክርስቲያኖች መዝናኛ ምን እንደሚሆን ገምታ ነበር?
-
ኒታ፣ ጄድን ከመጥፎ ጓደኝነት እንድትላቀቅና በምትኩ ጥሩ ጓደኞች እንድታፈራ የረዳቻት እንዴት ነው?