ክርስቲያናዊ ሕይወት
ወጣቶች፣ ለወላጆቻችሁ የልባችሁን አውጥታችሁ ንገሯቸው
ለወላጆቻችሁ የልባችሁን አውጥታችሁ ለመንገር ጥረት ማድረግ ያለባችሁ ለምንድን ነው? (ምሳሌ 23:26) ምክንያቱም ይሖዋ እናንተን እንዲንከባከቧችሁና እንዲመሯችሁ ኃላፊነት የሰጠው ለእነሱ ነው። (መዝ 127:3, 4) የሚያሳስባችሁንና የሚያስጨንቃችሁን ነገር ከደበቃችኋቸው እናንተን መርዳት ይቸገራሉ። እናንተም ብትሆኑ ከእነሱ የሕይወት ተሞክሮ ትምህርት ማግኘት የምትችሉበት አጋጣሚ ያመልጣችኋል። ሆኖም አንዳንድ ነገሮችን ለራሳችሁ መያዛችሁ ስህተት ነው? ላይሆን ይችላል፤ ወላጆቻችሁን መዋሸት ወይም ሊያውቁ የሚገባቸውን መረጃ መደበቅ ግን የለባችሁም።—ምሳሌ 3:32
ታዲያ ወላጆቻችሁን ማናገር የምትችሉት እንዴት ነው? ለእናንተም ሆነ ለእነሱ አመቺ የሆነ ጊዜ ምረጡ። እንዲህ ማድረግ ከተቸገራችሁ ግን የሚሰማችሁን ነገር በደብዳቤ ልትገልጹላቸው ትችላላችሁ። ወላጆቻችሁ እናንተ ማንሳት ስለማትፈልጉት ርዕሰ ጉዳይ ሊያወሯችሁ ቢፈልጉስ? ዋነኛ ፍላጎታቸው እናንተን መርዳት መሆኑን አትርሱ። ወላጆቻችሁ አጋሮቻችሁ እንጂ ጠላቶቻችሁ እንዳልሆኑ አስታውሱ። ከወላጆቻችሁ ጋር በግልጽ ለመነጋገር የምታደርጉት ጥረት በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ ይጠቅማችኋል፤ ወደፊት ደግሞ የዘላለም ሕይወት ያስገኝላችኋል።—ምሳሌ 4:10-12
የወጣትነት ሕይወቴ—ከወላጆቼ ጋር መግባባት የምችለው እንዴት ነው? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
ኤስተር እና ፓትሪክ በኋላ ላይ ስለ ራሳቸው ምን ተገንዝበዋል?
-
ኢየሱስ ከተወው ምሳሌ ምን ትማራላችሁ?
-
ወላጆቻችሁ ከልብ እንደሚያስቡላችሁ ያሳዩት እንዴት ነው?
-
ወላጆቻችሁን ለማነጋገር ጥረት ስታደርጉ የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ሊረዷችሁ ይችላሉ?