በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ቭላድሚር ሱቮሮቭ እና ባለቤታቸው እህት ቫለንቲና

ሰኔ 15, 2021
ሩሲያ

በቼልያቢንስክ የሚኖሩ የሰባ አምስት ዓመት አረጋዊ ወንድም በሃይማኖታቸው ምክንያት ስደት እየደረሰባቸው ነው

በቼልያቢንስክ የሚኖሩ የሰባ አምስት ዓመት አረጋዊ ወንድም በሃይማኖታቸው ምክንያት ስደት እየደረሰባቸው ነው

ወቅታዊ መረጃ | የሩሲያ ፍርድ ቤት የይግባኝ ጥያቄውን ውድቅ አደረገ

ጥቅምት 15, 2021 የቼልያቢንስክ ክልል የወንድም ሱቮሮቭን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። ቀደም ሲል የተላለፈባቸው ፍርድ በዚያው ይጸናል። እርግጥ ወንድም ቭላድሚር አሁን ወህኒ አይወርዱም።

ሐምሌ 1, 2021 በቼልያቢንስክ የሚገኘው የሜተለርጂቼስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት የ75 ዓመት አረጋዊ የሆኑት ወንድም ቭላድሚር ሱቮሮቭ ጥፋተኛ ናቸው በማለት የስድስት ዓመት የገደብ እስራት በይኖባቸዋል።

አጭር መግለጫ

ቭላድሚር ሱቮሮቭ

  • የትውልድ ዘመን፦ 1946 (ቼልያቢንስክ)

  • ግለ ታሪክ፦ የፋብሪካ ሠራተኛ ነበሩ፤ ቲያትር ቤት ተዋናይ ሆነውም ሠርተዋል። በተጨማሪም የሶቪየት የባሕል ማዕከል ውስጥ አስተዳዳሪ ሆነው ሠርተዋል። ሙዚቃ መድረስ እንዲሁም ጊታር መጫወት ይወዳሉ

    በ1973 ከቫለንቲና ጋር ትዳር መሠረቱ። በ1993 ተጠመቁ። ባልና ሚስቱ ኢጎር የተባለ ልጅ የነበራቸው ቢሆንም በ2014 በካንሰር ሕይወቱ አልፏል

የክሱ ሂደት

ጥር 16, 2020 በቼልያቢንስክ ያሉ ባለሥልጣናት በ75 ዓመቱ ወንድም ቭላድሚር ሱቮሮቭ ላይ ምርመራ ማድረግ ጀመሩ። የቼልያቢንስክ ክልል መርማሪ፣ ወንድም ቭላድሚርን ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎችን አደራጅተዋል በሚል ከሰሳቸው፤ ከተከሰሱባቸው ነገሮች መካከል ሃይማኖታዊ መዝሙሮችን መዘመር፣ መጸለይ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ውይይት ማድረግ ይገኙበታል።

የካቲት 2020 ባለሥልጣናቱ በወንድም ቭላድሚር ላይ የወንጀል ምርመራ ማድረግ ጀመሩ፤ የጉዞ እገዳም ጣሉባቸው። ሰኔ 17, 2020 ወንጀል ሠርተዋል ተብለው ተከሰሱ። ወንድም ቭላድሚር፣ ይህ ስደት ያስከተለባቸው መከራ በሕይወታቸው ውስጥ ካጋጠሟቸው በጣም ከባድ ፈተናዎች አንዱ እንደሆነ ገልጸዋል። አክለውም እንዲህ ብለዋል፦ “አምላካችን ይሖዋ ፈጽሞ አልተወንም። . . . ከይሖዋ ጋር ያለን ግንኙነት በየጊዜው ይበልጥ እየተጠናከረ ነው። እኔና ቫለንቲና የይሖዋን እጅ አይተናል። ይሖዋ ውድ በሆኑት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን አማካኝነት ያበረታታናል፤ ያጠነክረናል እንዲሁም ያጽናናናል፤ ሌላ ጉባኤ ውስጥ ያሉ ወንድሞችም ጭምር አበረታተውናል።”

የወንድም ቭላድሚርን ጉዳይ እየተመለከተ ያለው ፍርድ ቤት የ73 ዓመት አረጋዊት በሆኑት በእህት ቫለንቲና ላይ መጋቢት 11, 2021 የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ፈርዶባቸዋል። ሁለቱም a ይሖዋ ምንጊዜም ከጎናቸው ሆኖ እንደሚደግፋቸው እርግጠኞች ናቸው።—መዝሙር 118:6

a ከወንድም ቭላድሚር እና ከእህት ቫለንቲና ሱቮሮቭ ጋር የተደረገውን ቃል ምልልስ በ2021 የበላይ አካሉ ሪፖርት ቁጥር 4 (10:02) ላይ ይገኛል።