በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም አንድሬ ማርቲኖቭ፣ ባለቤቱ ኒና፣ እህት ዞያ ፓቭሎቫ እና ወንድም ሚኻይል ዬርማኮቭ

ታኅሣሥ 8, 2022 | የታደሰው፦ የካቲት 15, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—መቀጮው ተቀነሰ | በይሖዋ ድጋፍ መተማመን

ወቅታዊ መረጃ—መቀጮው ተቀነሰ | በይሖዋ ድጋፍ መተማመን

የካቲት 13, 2023 የቹቫሽ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በእህት ኒና ማርቲኖቫ እና በእህት ዞያ ፓቭሎቫ ላይ የተጣለው የገንዘብ መቀጮ ከ350,000 ሩብል (4,780 የአሜሪካ ዶላር) ወደ 80,000 ሩብል (1,092 የአሜሪካ ዶላር) እንዲቀነስ ወስኗል። በወንድም አንድሬ ማርቲኖቭ እና በወንድም ሚኻይል ዬርማኮቭ ላይ የተላለፈው የገደብ እስራት ግን አልተቀየረም።

ታኅሣሥ 22, 2022 በቹቫሽ ሪፑብሊክ የሚገኘው የአላቲርስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በአንድሬ፣ በኒና፣ በዞያ እና በሚኻይል ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ኒና እና ዞያ 350,000 ሩብል (4,780 የአሜሪካ ዶላር) የገንዘብ መቀጮ እንዲከፍሉ ተወስኗል። አንድሬ እና ሚኻይል ደግሞ ስድስት ዓመት የገደብ እስራት ተበይኖባቸዋል። በእርግጥ አሁን ወህኒ አይወርዱም።

አጭር መግለጫ

በስደት እየጸኑ እንዳሉት ታማኝ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሁሉ እኛም “እንደ አንበሳ ልበ ሙሉ” መሆን እንችላለን፤ የይሖዋ ፍቅርና ድጋፍ ስለማይለየን ፈተናዎችን በጽናት እንወጣለን።—ምሳሌ 28:1

የክሱ ሂደት

  1. ሰኔ 23, 2021

    አላቲር ውስጥ ብዙ ቤቶች ተፈተሹ

  2. ጥቅምት 28, 2021

    አንድሬ የጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴዎችን አስተባብረሃል ተብሎ የወንጀል ምርመራ ይደረግበት ጀመር። የጉዞ ክልከላዎች ተጣሉበት

  3. ሚያዝያ 25, 2022

    አንድሬ በይፋ ክስ ተመሠረተበት። ኒናም በክሱ መዝገብ ውስጥ ተካተተች፤ የተከሰሰችውም በጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴ ተሳትፋለች በሚል ነው

  4. ሚያዝያ 26, 2022

    ዞያ በጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴ ተሳትፋለች በሚል በይፋ ከተከሰሰች በኋላ በክስ መዝገቡ ውስጥ ተካተተች

  5. ሚያዝያ 28, 2022

    ሚኻይል የጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴዎችን አስተባብሯል በሚል በይፋ ከተከሰሰ በኋላ በክስ መዝገቡ ውስጥ ተካተተ

  6. ነሐሴ 31, 2022

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ