ግንቦት 25, 2022
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ | “ምን የሚያስፈራኝ ነገር አለ?”
ግንቦት 25, 2022 በቼልያቢንስክ የሚገኘው የሜተለርጂቼስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ፓቬል ፖፖቭ ጥፋተኛ ነው ብሎ የስድስት ዓመት የገደብ እስር ፈርዶበታል። እርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።
የክሱ ሂደት
መጋቢት 26, 2019
ጭንብል ያጠለቁ እንዲሁም አውቶማቲክ ጠመንጃና ትልቅ መዶሻ የያዙ አሥር ሰዎች የፓቬልን ቤት ሰብረው ገብተው በረበሩ
ሚያዝያ 22, 2021
የወንጀል ክስ ተመሠረተበት
ግንቦት 18, 2021
ፖሊሶች ለሁለተኛ ጊዜ የፓቬልን ቤት ፈተሹ። የፓቬል ባለቤት የሌና እና የ13 ዓመት ሴት ልጃቸው ለምርመራ ተወሰዱ
ነሐሴ 31, 2021
የሽብርተኞችና የጽንፈኞች ስም ዝርዝር በሚገኝበት መዝገብ ላይ ተካተተ
ኅዳር 29, 2021
ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
ወንድሞቻችን ከአቋማቸው ፍንክች ሳይሉ ፈተናን በድፍረት መጋፈጣቸውን ቀጥለዋል፤ ይሖዋም እነዚህን ታማኝ አገልጋዮቹን እንደሚደግፋቸውና ወሮታቸውን እንደሚከፍላቸው እርግጠኞች ነን።—2 ሳሙኤል 22:19-21