ሚያዝያ 1, 2024 | የታደሰው፦ ሐምሌ 30, 2024
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ሦስት የይሖዋ ምሥክሮች ተፈረደባቸው | “እጅ መስጠት አማራጭ አይደለም”
ሐምሌ 30, 2024 በካባሮቭስክ ግዛት የሚገኘው የኒኮላዬቭስክ ኦን አሙር ከተማ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ኢጎር ክሌትኪን፣ ወንድም ኒኮላይ ኮኖኔንኮ እና እህት ናዴዥዳ ኮሮቦችኮ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ኢጎር እና ኒኮላይ የስድስት ዓመት ናዴዥዳ ደግሞ የአምስት ዓመት የገደብ እስራት ተበይኖባቸዋል።አሁን ወህኒ አይወርዱም።
አጭር መግለጫ
ይሖዋ የሚታመኑበትን እና “አንተ አምላኬ ነህ” የሚሉትን ሁሉ በፍቅር ስለሚንከባከብና ስለሚደግፋቸው እናመሰግነዋለን።—መዝሙር 31:14
የክሱ ሂደት
ጥቅምት 11, 2021
የኢጎር እና የናዴዥዳ ቤቶች ተፈተሹ። ኢጎር ጣቢያ እንዲያድር ተደረገ
ጥቅምት 12, 2021
ናዴዥዳ ምርመራ ተደረገባት
ጥቅምት 13, 2021
ኢጎር ከጣቢያ ተለቀቀ
ጥቅምት 14, 2021
ኢጎር እና ናዴዥዳ የጉዞ ገደቦች ተጣሉባቸው
መስከረም 27, 2022
ኒኮላይ የጉዞ ገደቦች ተጣሉበት
ጥር 16, 2023
ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ