በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በስተ ግራ፦ ወንድም አናቶሊ ጌዚክ እና ባለቤቱ ኢሪና። በስተ ቀኝ፦ ወንድም ቪክቶር ዚሞቭስኪ እና ባለቤቱ ናዴዥዳ

ነሐሴ 26, 2022 | የታደሰው፦ መጋቢት 8, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ብይኑ ተቀየረ | በእርጋታና በእምነት ስደትን መጋፈጥ

ወቅታዊ መረጃ—ብይኑ ተቀየረ | በእርጋታና በእምነት ስደትን መጋፈጥ

መጋቢት 1, 2023 የስታቭሮፖል ክልል ፍርድ ቤት ከወንድም አናቶሊ ጌዚክ እና ከባለቤቱ ከኢሪና እንዲሁም ከወንድም ቪክቶር ዚሞቭስኪ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ውሳኔውን አሳውቋል። ቀደም ሲል በአናቶሊ እና በቪክቶር ላይ የተላለፈው ብይን ወደ ገደብ እስራት ተቀይሯል። በመሆኑም አናቶሊ የጉልበት ሥራ በሚሠራበት እስር ቤት የጉልበት ሥራ ለመሥራት አይገደድም። ቪክቶር ወዲያውኑ ከእስር ቤት ተለቅቋል። የኢሪና የገደብ እስራት ፍርድ አልተለወጠም። ሆኖም አሁን ወህኒ አትወርድም።

ኅዳር 14, 2022 በስታቭሮፖል ክልል የሚገኘው የጌኦርጊዬቭስኪ ከተማ ፍርድ ቤት በአናቶሊ እና በባለቤቱ በኢሪና እንዲሁም በቪክቶር ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። አናቶሊ የጉልበት ሥራ በሚሠራበት እስር ቤት ውስጥ የአራት ዓመት ከሁለት ወር እስራት ተፈርዶበታል። ኢሪና የአራት ዓመት ከሁለት ወር የገደብ እስራት ተላልፎባታል። ቪክቶር ደግሞ በስድስት ዓመት ከሁለት ወር እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል፤ ከዚያው ከፍርድ ቤት ወደ እስር ቤት ተወስዷል።

የክሱ ሂደት

  1. ጥቅምት 23, 2019

    ፖሊሶች በጌኦርጊዬቭስክ በሚገኙ ሦስት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ላይ ፍተሻ አደረጉ። ፖሊሶቹ ፍተሻ በሚያደርጉበት ወቅት በእነዚህ የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ውስጥ በኋላ እንደ ማስረጃ ሊያቀርቧቸው የሚችሏቸው ነገሮችን ደበቁ። አናቶሊ፣ ኢሪና፣ ቪክቶር እና ሌሎች ስምንት የይሖዋ ምሥክሮች ሌሊቱን ተይዘው ምርመራ ተደረገባቸው

  2. ታኅሣሥ 30, 2019

    በአናቶሊ፣ በኢሪና እና በቪክቶር ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተ

  3. ጥር 23, 2020

    ቪክቶር ለተጨማሪ ምርመራ ከተጠራ በኋላ በጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ እንዲቆይ ተደረገ። በቀጣዩ ቀን ማረፊያ ቤት ገባ

  4. መጋቢት 23, 2020

    ቪክቶር ከማረፊያ ቤት ተለቆ የቁም እስረኛ እንዲሆን ተደረገ

  5. ግንቦት 6, 2020

    ቪክቶር ከቁም እስር ነፃ የተደረገ ቢሆንም የጉዞ ገደብ ተጣለበት

  6. ጥቅምት 6, 2021

    ቪክቶር የተጣለበት የጉዞ ገደብ ተነሳለት

  7. መጋቢት 10, 2022

    ክሱ መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ወንድሞቻችን ስደትን በደስታና በተስፋ እየተቋቋሙ ባሉበት በዚህ ጊዜ ይሖዋ “ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ” መሆኑን እንደሚያሳያቸው እንተማመናለን።—መዝሙር 145:18