ጥር 4, 2023 | የታደሰው፦ ኅዳር 17, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—እህታችን ተፈረደባት | ስደት ቢደርስባትም ሌሎችን ለመርዳት ቆርጣለች
ኅዳር 15, 2023 በኖቮኩዝኔትስክ የሚገኘው የኩዝኔትስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት እህት ታትያና ሱሺልኒኮቫ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን በማስተላለፍ የአራት ዓመት የገደብ እስራት ፈርዶባታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አትወርድም።
አጭር መግለጫ
እንደ ታትያና ሁሉ እኛም በይሖዋ እርዳታ ስደትን የተጋፈጡት “ታላቅ የምሥክሮች ደመና” የተዉትን ምሳሌ በመመርመር ብርታት እናገኛለን።—ዕብራውያን 12:1
የክሱ ሂደት
ሰኔ 8, 2021
የታጠቁ የፌዴራል ደህንነት አባላት በኖቮኩዝኔትስክ የሚገኙ ሦስት የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች በረበሩ። ታትያና እና ባለቤቷ ሰርጌ ለሦስት ሰዓት ምርመራ ተደረገባቸው
ሰኔ 20, 2022
ክስ ተመሠረተባት። ክሷ ‘ሃይማኖታዊ ውይይት አድርገሻል እንዲሁም በስብሰባዎች ላይ ተሳትፈሻል’ የሚል ነው
ሐምሌ 22, 2022
በይፋ ክስ ተመሠረተባት
መስከረም 27, 2022
ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ። ዳኛው፣ የአሠራር ጥሰት ተፈጽሟል በማለት ክሱ ወደ አቃቤ ሕግ እንዲመለስ አደረጉ
ኅዳር 16, 2022
ክሷ በድጋሚ መታየት ጀመረ