የካቲት 21, 2024 | የታደሰው፦ መጋቢት 25, 2024
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—እህት ተፈረደባት | በሚያበረታቱ ወንድሞችና እህቶች ተከብቤያለሁ
መጋቢት 22, 2024 የቶልያቲ ማዕከላዊ የአውራጃ ፍርድ ቤት፣ እህት ዬሌና ዩሬንኮቫ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን አስተላልፏል፤ የሁለት ዓመት የገደብ እስራትም ፈርዶባታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አትወርድም።
አጭር መግለጫ
ይሖዋን ‘እጅ ለእጅ ተያይዘን እያገለገልን’ ባለንበት በዚህ ወቅት እሱ ዬሌናንም ሆነ ስደትን በጽናት እየተጋፈጡ ያሉትን ሁሉ በፍቅሩ እየተንከባከበ በመሆኑ አመስጋኞች ነን።—ሶፎንያስ 3:9
የክሱ ሂደት
ግንቦት 15, 2023
የክስ ፋይል ተከፈተባት
ግንቦት 16, 2023
ቤቷ ተፈተሸ። ምርመራ ከተደረገባት በኋላ የጉዞ ገደብ ተጣለባት
ሰኔ 5, 2023
የወንጀል ክስ ተመሠረተባት
ነሐሴ 23, 2023
ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ