ግንቦት 1, 2024 | የታደሰው፦ ሐምሌ 9, 2024
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—እህት ተፈረደባት | “ከዚህ የተለየ ሕይወት መኖር አልፈልግም”
ሐምሌ 8, 2024 በሰማረ ክልል፣ በቶልያቲ ከተማ የሚገኘው የሴንትራልኒ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ እህት ጋሊና ኮሚሳሮቫ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን አስተላልፏል። የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶባታል። አሁን ወህኒ አትወርድም።
አጭር መግለጫ
እንደ ጋሊና ሁሉ እኛም ‘የይሖዋ እንደሆንን’ ስለምናውቅ እሱን የማወቅና የማገልገል መብታችንን ከፍ አድርገን እንመለከተዋለን።—ሮም 14:8
የክሱ ሂደት
መስከረም 7, 2023
የክስ ፋይል ተከፈተባት
መስከረም 8, 2023
ቤቷ ተፈተሸ፤ ምርመራም ተደረገባት
መስከረም 19, 2023
የጉዞ ገደብ ተጣለባት
ታኅሣሥ 18, 2023
ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ