ግንቦት 16, 2022 | የታደሰው፦ ሚያዝያ 3, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—እስራት ተፈረደበት | ሰርጌ አናኒን በአምላክ ላይ ያለው እምነት ተጠናክሯል
መጋቢት 31, 2023 በኬሜሮቮ ክልል የሚገኘው የቤሎቮ ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም ሰርጌ አናኒን ጥፋተኛ ነው በማለት የስድስት ዓመት እስራት በይኖበታል። ሰርጌ ከፍርድ ቤት በቀጥታ ወህኒ ወርዷል።
የክሱ ሂደት
የካቲት 9, 2021
የወንጀል ክስ ተመሠረተበት። የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴዎች አስተባብረሃል በሚል ተከሰሰ
የካቲት 14, 2021
ተይዞ ማረፊያ ቤት እንዲቆይ ተደረገ
የካቲት 16, 2021
የቁም እስረኛ ተደረገ
ጥር 25, 2022
ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
ይሖዋ አምላክ በሩሲያም ሆነ በምድር ዙሪያ ላሉ ታማኝ አገልጋዮቹ ፍቅሩን፣ ድጋፉንና በረከቱን አትረፍርፎ እንደሚያፈስላቸው እርግጠኞች ነን።—ሚልክያስ 3:10