በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ እህት ልዩቦቭ ጋሊትሲና፣ ወንድም ጋሬጊን ኻቻቱርያን እና ወንድም ጌቮርግ ዬሪትስያን

ሚያዝያ 8, 2024 | የታደሰው፦ ሐምሌ 1, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—እስራት ተፈረደባቸው | ማረፊያ ቤት ውስጥ የይሖዋን እንክብካቤ መቅመስ

ወቅታዊ መረጃ—እስራት ተፈረደባቸው | ማረፊያ ቤት ውስጥ የይሖዋን እንክብካቤ መቅመስ

ሰኔ 26, 2024 በሮስቶቭ ክልል የሚገኘው የኖቮቼርካስክ ከተማ ፍርድ ቤት፣ እህት ልዩቦቭ ጋሊትሲና፣ ወንድም ጋሬጊን ኻቻቱርያን እና ወንድም ጌቮርግ ዬሪትስያን ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። እህት ልዩቦቭ የሁለት ዓመት ከሦስት ወር እስራት ተፈርዶባታል፤ ሆኖም ማረፊያ ቤት ካሳለፈችው ጊዜ አንጻር የእስራት ጊዜዋን እንደጨረሰች ተቆጥሮላታል። አሁን ወህኒ አትወርድም። ጋሬጊን የስድስት ዓመት ከስድስት ወር፣ ጌቮርግ ደግሞ የስድስት ዓመት ከሁለት ወር እስራት ተበይኖባቸዋል። ወንድሞች እስር ቤት ይቆያሉ።

አጭር መግለጫ

ተቃዋሚዎቻችን ጉዳት ሊያደርሱብን ቢያስቡም ይሖዋ ታማኝ አገልጋዮቹን መባረኩን እንደሚቀጥልና “ነገሩን ለመልካም [እንደሚያደርገው]” እንተማመናለን።​—ዘፍጥረት 50:20

የክሱ ሂደት

  1. ነሐሴ 11, 2022

    ልዩቦቭ፣ ጋሬጊን እና ጌቮርግ የክስ ፋይል ተከፈተባቸው። ቤቶቻቸው ተፈተሹ። ጋሬጊን እና ጌቮርግ ጣቢያ ተወሰዱ

  2. ነሐሴ 12, 2022

    ጋሬጊን እና ጌቮርግ ማረፊያ ቤት ገቡ

  3. ነሐሴ 16, 2022

    ልዩቦቭ ጣቢያ ተወሰደች

  4. ነሐሴ 17, 2022

    ልዩቦቭ ማረፊያ ቤት ገባች

  5. መስከረም 20, 2023

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  6. ታኅሣሥ 25, 2023

    ልዩቦቭ ከማረፊያ ቤት ተለቀቀች፤ የቁም እስረኛ ሆነች

a b ይህ ዜና በተጠናቀረበት ወቅት ወንድም ጋሬጊን እና ወንድም ጌቮርግ ማረፊያ ቤት ስለነበሩ አስተያየታቸውን ማግኘት አልተቻለም