ነሐሴ 30, 2022 | የታደሰው፦ ነሐሴ 8, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድም መቀጮ ተጣለበት | “በይሖዋ ላይ ያለኝን እምነት መገንባት”
ነሐሴ 3, 2023 ካባረቭስክ ክልል የሚገኘው የቢኪንስኪ ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም ሰርጌ ካዛኮቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል። ሰርጌ የ500,000 ሩብል (5,186 የአሜሪካ ዶላር) መቀጮ ተጥሎበታል።
የክሱ ሂደት
ኅዳር 9, 2020
የወንጀል ክስ ተመሠረተበት። የጽንፈኛ ድርጀት እንቅስቃሴን በማስተባበር ወንጀል ተከሰሰ
ታኅሣሥ 21, 2020
የምርመራ ኮሚቴውና የደህንነት ቢሮ ሠራተኞች የሰርጌን ቤት ጨምሮ አሥር ቤቶችን ፈተሹ። ሰርጌ ተይዞ በጊዜያዊ ማቆያ እንዲቆይ ተደረገ
ታኅሣሥ 23, 2020
ወደ ማረፊያ ቤት ተላከ
ሰኔ 4, 2021
ከማረፊያ ቤት እንዲወጣና በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ
ነሐሴ 5, 2021
ከቁም እስር ተለቀቀ
የካቲት 28, 2022
ክሱ መታየት ጀመረ። ክሱ መጀመሪያ ላይ በፍርድ ቤት በታየበት ጊዜ ዳኛው አቃቤ ሕጉ በክስ ሂደቱ ላይ ስህተት እንደሠራ በመግለጽ ጉዳዩን ወደ አቃቤ ሕግ መለሰው
ሚያዝያ 28, 2022
ዳኛው ጉዳዩ ወደ አቃቤ ሕግ እንዲመለስ የተላለፈውን ብይን በመቀልበስ የመጀመሪያው ፍርድ ቤት ድጋሚ ክሱን እንዲያይ አደረገ
ሰኔ 14, 2022
ክሱ ድጋሚ መታየት ጀመረ
አጭር መገለጫ
ሰርጌ በይሖዋ ላይ ያለውን እምነት ማሳየቱን ቀጥሏል፤ እኛም ልክ እንደ እሱ በመዝሙር 31:14 ላይ ያለውን የሚከተለውን ሐሳብ እናስተጋባለን፦ “ይሖዋ ሆይ፣ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ። ‘አንተ አምላኬ ነህ’ እላለሁ።”