ሰኔ 8, 2022
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተለቀቀ | የእምነት አጋሮቻቸው ደግፈዋቸዋል
ኅዳር 10, 2022 የቮልጎዳ ክልላዊ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ዩሪ ባራኖቭ እና ወንድም ኒኮላይ ስቴፓኖቭ ያቀረቡትን ይግባኝ ተመልክቶ ውሳኔ አስተላልፏል። በዩሪ ብይን ላይ ለውጥ አልተደረገም። በኒኮላይ ላይ ተላልፎ የነበረው የአራት ዓመት እስራት ግን ወደ አራት ዓመት የገደብ እስራት እንዲቀነስ ተወስኗል። ኒኮላይ ወዲያውኑ ከእስር ተለቋል።
መስከረም 5, 2022 የቮልጎዳ ከተማ ፍርድ ቤት ዩሪ እና ኒኮላይ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ዩሪ የአራት ዓመት የገደብ እስራት ተፈረደበት። በእርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም። ኒኮላይ የአራት ዓመት እስራት የተፈረደበት ሲሆን ወዲያውኑ ወህኒ ወርዷል።
የክሱ ሂደት
ታኅሣሥ 19, 2019
የደህንነት አባላት ቮልጎዳ ውስጥ የስድስት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶችን በረበሩ። ዩሪ እና ኒኮላይ ጣቢያ ተወሰዱና በዚያ እንዲቆዩ ተደረገ
ታኅሣሥ 20, 2019
ዩሪ ተፈትቶ የቁም እስረኛ ተደረገ
ታኅሣሥ 23, 2019
ኒኮላይ ማረፊያ ቤት ገባ
መጋቢት 16, 2020
ዩሪ ከቁም እስር ነፃ ተደረገ፤ ሆኖም በክስ ፋይሉ ከተካተቱ ሰዎች ጋር እንዳይገናኝ እንዲሁም ስልክና ኢንተርኔት እንዳይጠቀም ክልከላዎች ተጣሉበት
ግንቦት 19, 2020
በዩሪ ላይ የተጣሉት ክልከላዎች ተነሱለት
ነሐሴ 13, 2020
ኒኮላይ ከማረፊያ ቤት ተፈትቶ የቁም እስረኛ ተደረገ
መስከረም 25, 2020
ኒኮላይ ከቁም እስር ነፃ ተደረገ
መጋቢት 7, 2022
ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
ወንድሞቻችን ዛሬም ለስደት አልተንበረከኩም፤ ታማኝነታቸውን ማየት በእርግጥም እምነት ያጠነክራል።—1 ተሰሎንቄ 3:7