ኅዳር 25, 2022| የታደሰው፦ ታኅሣሥ 8, 2022
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “ብቻችንን እንዳልሆንን እናውቃለን”
ታኅሣሥ 7, 2022 በቼልያቢንስክ ከተማ የሚገኘው የሜታለርጂቼስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ቫዲም ጊዛቱሊን ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ቫዲም የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶበታል። በእርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።
አጭር መግለጫ
እኛም ፈተናዎች ሲያጋጥሙን መቼም ብቻችንን እንዳልሆንን እርግጠኞች እንሁን። ይሖዋ ታማኝ አገልጋዮቹን ፈጽሞ አይተዋቸውም።—መዝሙር 9:9, 10
የክሱ ሂደት
መጋቢት 26, 2019
በወንድም ቭላድሚር ሱቮሮቭ ላይ ከተከፈተው የክስ መዝገብ ጋር ተያይዞ መኖሪያ ቤቱ ተፈተሸ
ነሐሴ 31, 2021
በቫዲም ላይ ክስ ተመሠረተበት። በታገደ ሃይማኖታዊ ድርጅት እንቅስቃሴ ተሳትፈሃል ተብሎ ተከሰሰ
ጥቅምት 22, 2021
መኖሪያ ቤቱ ለሁለተኛ ጊዜ ተፈተሸ። ቫዲምና ባለቤቱ ለምርመራ ተወሰዱ
ሐምሌ 14, 2022
የጉዞ እገዳ ተጣለበት
ነሐሴ 18, 2022
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ