ነሐሴ 10, 2022
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | ቪክቶር ሻያፖቭ አድናቂ መሆኑ በደስታ እንዲጸና ረድቶታል
ኅዳር 7, 2022 በፔንዛ ክልል የሚገኘው የኒኮልስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ቪክቶር ሻያፖቭን ጥፋተኛ ነው በማለት የሁለት ዓመት የገደብ እስራት በይኖበታል። በእርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።
የክሱ ሂደት
ነሐሴ 19, 2021
በጽንፈኝነት እንቅስቃሴዎች ተሳትፈሃል በሚል የወንጀል ክስ ተመሠረተበት።
የካቲት 5, 2022
ፖሊሶች መንገድ ላይ ይዘው በቁጥጥር ስር ካዋሉት በኋላ በዚያኑን ዕለት ቤቱን ሰብረው በመግባት በረበሩ። ከዚያም 740 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ወደ ፔንዛ ተወሰደ
የካቲት 6, 2022
ማረፊያ ቤት እንዲገባ ተደረገ
የካቲት 8, 2022
ከማረፊያ ቤት ተለቆ የቁም እስረኛ እንዲሆን ተደረገ
መጋቢት 28, 2022
ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
ስደት በሚደርስብን ወቅት የይሖዋ ፍቅራዊ ደግነት የሚያስገኝልን ሰላም ልብና አእምሯችንን እንደሚጠብቅል ማወቃችን በአመስጋኝነት መንፈስ እንድሞላ ያደርገናል።—ፊልጵስዩስ 4:7