ነሐሴ 31, 2022 | የታደሰው፦ ጥር 26, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | ‘ይሖዋ ያለአንዳች ፍርሃት ከጎኔ የሚቆሙ ወዳጆች ሰጥቶኛል’
ጥር 24, 2023 በኬሜሮቮ ክልል፣ በኖቮኩዝኔትስክ የሚገኘው የኩዝንዬትስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ሰርጌ ሱሺልኒኮቭ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶበታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።
የክሱ ሂደት
ኅዳር 2019
መርማሪዎች የሰርጌን የስልክ ውይይቶች ጠልፈው ማዳመጥና ቤቱን በካሜራ መከታተል ጀመሩ
ሰኔ 3, 2021
የወንጀል ክስ ተመሠረተ
ሰኔ 8, 2021
ቤቱ ተፈተሸ። ሰርጌና ባለቤቱ ለምርመራ ተወሰዱ
ሐምሌ 15, 2021
በፌዴራል የአሸባሪዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተተ ሲሆን የባንክ ሒሳቡ እንዳይንቀሳቀስ ታገደ
የካቲት 8, 2022
የአንድን ጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴ በማስተባበርና በማስቀጠል ወንጀል ተከሰሰ። የጉዞ ገደብ ተጣለበት
መጋቢት 30, 2022
ክሱ መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
ይሖዋ “በጭንቅ ጊዜ” ሁሉ ታማኝ አገልጋዮቹን እንደሚረዳቸው ማወቃችን በጣም ያጽናናናል።—መዝሙር 46:1