ግንቦት 18, 2022 | የታደሰው፦ መጋቢት 12, 2024
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ታሰረ | ኢንቨር ሲዩኮቭ በብርታት ተሞልቷል
መጋቢት 7, 2024 በአድጄያ ሪፑብሊክ የሚገኘው የማይኮፕ ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም ኢንቨር ሲዩኮቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን በማስተላለፍ በስድስት ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኗል። ከሚያዝያ 2021 ጀምሮ ማረፊያ ቤት የነበረ ሲሆን እስራቱ በዚሁ ይቀጥላል።
የክሱ ሂደት
ሚያዝያ 15, 2021
በቪዲዮ ኮንፈረንስ ስብሰባ አድርጓል ተብሎ ተከሰሰ
ሚያዝያ 16, 2021
ፖሊሶች የኢንቨርን እና የሌሎች አራት የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች ፈተሹ። ምርመራ ተደረገበት፤ ለጊዜው ጣቢያ ውስጥ እንዲቆይ ተደረገ
ሚያዝያ 17, 2021
ማረፊያ ቤት ተላከ
ነሐሴ 15, 2021
ከማይኮፕ 110 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኝ ከፍተኛ ጥበቃ ወደሚደረግበት ማረፊያ ቤት ተላከ
መስከረም 13, 2021
ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
ውድ የሩሲያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ‘ከጌታና ከታላቅ ብርታቱ ኃይል ማግኘታቸውን እንደሚቀጥሉ’ እንተማመናለን።—ኤፌሶን 6:10
a ወንድም ሲዩኮቭ አሁን የሚገኘው ማረፊያ ቤት ስለሆነ የግል አስተያየቱን ማግኘት አልተቻለም።