ጥር 13, 2022
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ | ወንድም ዬቭስቲግኔቭ በይሖዋ መተማመኑ ታማኝ እንዲሆን ረድቶታል
ነሐሴ 1, 2022 የኒዥኒ ኖቭጎሮድ ክልላዊ ፍርድ ቤት ወንድም ኪሪል ዬቭስቲግኔቭ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አድርጓል። እርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።
ግንቦት 12, 2022 በኒዥኒ ኖቭጎሮድ ከተማ የሚገኘው የሌኒንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ኪሪል ጥፋተኛ ነው በማለት የሦስት ዓመት የገደብ እስራት በየነበት።
የክሱ ሂደት
ጥቅምት 8, 2021
ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ። ኪሪል ለዳኛው በሰጠው ሐሳብ ላይ ዝግጅቱ ማኅበራዊ እንጂ ሃይማኖታዊ እንዳልሆነ አብራራ
ነሐሴ 24, 2021
በኪሪል ላይ የጉዞ እገዳ ተጣለበት
መስከረም 2, 2020
ኪሪል የመሰብሰቢያ አዳራሹን በመከራየቱ “የጽንፈኝነት እንቅስቃሴዎችን በገንዘብ በመደገፍ” ተከሰሰ
ሐምሌ 11, 2019
ባለሥልጣናቱ በኪሪል ላይ ያተኮሩት ለመሰብሰቢያ አዳራሹ ውል የተፈራረመው እሱ ስለሆነ ነው፤ ቤቱ ተፈተሸ
ሰኔ 4, 2019
በዝግጅቱ ምክንያት “ማንነታቸው ባልተገለጸ” ሰዎች ላይ የወንጀል ምርመራ ተከፈተ
ሚያዝያ 2019
ኪሪል እና በኒዥኒ ኖቭጎሮድ የሚኖሩ ሌሎች የይሖዋ ምሥክሮች ለአንድ ማኅበራዊ ዝግጅት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተከራዩ
አጭር መግለጫ
ኪሪል፣ ባለቤቱ እንዲሁም በሩሲያ እና በክራይሚያ ስደት እየደረሰባቸው ያሉት ታማኝ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሙሉ ስለሚያሳዩት ድፍረት መስማታችን ያበረታታናል።—ፊልጵስዩስ 1:13, 14