ሰኔ 1, 2022 | የታደሰው፦ መስከረም 6, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ተፈረደባቸው | የይሖዋ ድጋፍ ስላልተለያቸው በአቋማቸው ጸንተዋል
መስከረም 5, 2023 በታታርስታን ሪፑብሊክ የሚገኘው የኒዥኔካምስክ ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም ዴኒስ ፊላቶቭ፣ ወንድም ስታኒስላቭ ክልዩቺንኮቭ እና ወንድም ድሚትሪ ያርቻክ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። እያንዳንዳቸው የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል። አሁን ወህኒ አይወርዱም።
የክሱ ሂደት
ኅዳር 18, 2020
የፌዴራል ደህንነት አባላትና የታጠቁ አድማ በታኝ ፖሊሶች በኒዥኔካምስክ ከተማ የሚገኙ የ12 የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች በረበሩ። ዘጠኝ ወንድሞችና ሦስት እህቶች ለምርመራ ተወሰዱ
ነሐሴ 24, 2021
የወንጀል ምርመራውን ተከትሎ ዴኒስ፣ ስታኒስላቭ እና ዲሚትሪ የጉዞ እገዳ ተጣለባቸው
ጥቅምት 7, 2021
ዴኒስ፣ ስታኒስላቭ እና ዲሚትሪ ክስ ተመሠረተባቸው። ክሳቸው “ለየት ያሉ ሃይማኖታዊ መዝሙሮች ዘምረዋል እንዲሁም ጸልየዋል” የሚል ነው
ጥር 27, 2022
ክሳቸው በታታርስታን ሪፑብሊክ ወደሚገኘው የኒዥኔካምስክ ከተማ ፍርድ ቤት ተላለፈ
አጭር መግለጫ
ወንድሞቻችን፣ ይሖዋ የሚያስፈልጋቸውን ብርታት እንደሚሰጣቸው ይተማመናሉ፤ መዝሙራዊው ዳዊት “አምላክ ከጎኔ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ” በማለት የተናገረውን ሐሳብ እንደሚጋሩት ምንም ጥርጥር የለውም።—መዝሙር 56:9