ሐምሌ 8, 2022 | የታደሰው፦ ግንቦት 13, 2024
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | ጸሎት ብርታት ሰጥቷቸዋል
ግንቦት 13, 2024 በኢዢፍስክ የሚገኘው የፐርቮማይስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ሰርጌ አሺክሚን፣ በወንድም ማክሲም ዴሬንድዬቭ እና በወንድም አሌክሳንደር ኩቲን ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ሦስቱም የሦስት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል። ከፍርድ ቤት በቀጥታ ወህኒ ወርደዋል።
የክሱ ሂደት
ሚያዝያ 14, 2021
የፌዴራል ደህንነት አባላት ቢያንስ 12 የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶችን ፈተሹ። ሰርጌ ለሰባት ሰዓታት ምርመራ ተደረገበት። ማክሲም እና አሌክሳንደር ተይዘው ጣቢያ ተወሰዱ
ሚያዝያ 15, 2021
ማክሲም እና አሌክሳንደር ማረፊያ ቤት እንዲገቡ ተደረጉ
ሚያዝያ 29, 2021
አሌክሳንደር ከማረፊያ ቤት ተለቀቀ
ግንቦት 14, 2021
አሌክሳንደር የቁም እስረኛ ተደረገ
ሐምሌ 9, 2021
ማክሲም ከማረፊያ ቤት ተፈትቶ የቁም እስረኛ ተደረገ
መጋቢት 14, 2022
የክሱ ሂደት በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
ወንድሞቻችን፣ ይሖዋ “እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ” በማለት በገባው ቃል በመተማመን የሚደርስባቸውን ግፍ እየተጋፈጡ ነው።—ኢሳይያስ 43:5