ግንቦት 5, 2022 | የታደሰው፦ ታኅሣሥ 26, 2022
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—የጥፋተኝነት ብይን ተላለፈበት | ይሖዋ ለሰርጌ ኩዝነትሶቭ ኃይል ሰጥቶታል
ታኅሣሥ 22, 2022 በካባረቭስክ ክልል የሚገኘው የቭያዜምስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ሰርጌ ኩዝነትሶቭን ጥፋተኛ ነው በማለት ሁለት ዓመት ከአምስት ወር የገደብ እስራት በይኖበታል። በእርግጥ አሁን ወህኒ አይወርድም።
የክሱ ሂደት
መስከረም 3, 2020
የፌዴራል ደህንነት አባላት የሰርጌን ቤት ፈተሹ። መጽሐፍ ቅዱስ፣ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች፣ ፍላሽ ዲስኮችና ጽሑፎች ወረሱ
ሚያዝያ 2, 2021
በሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ተካተተ። የባንክ ሒሳቡ ታገደ
ኅዳር 9, 2021
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
ይሖዋ ለስሙ ሲሉ የሚደርስባቸውን ስደት በጽናት እየተቋቋሙ ላሉት በሩሲያና በክራይሚያ ለሚገኙ ወንድሞችና እህቶች ኃይል እንደሚሰጣቸው እርግጠኞች ነን።—ራእይ 2:3