ታኅሣሥ 28, 2021
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ | ይሖዋ እንደሚደግፋቸው ሙሉ እምነት ያላቸው ታማኝ የይሖዋ ምሥክሮች
ሚያዝያ 4, 2022 በካካሲያ ሪፑብሊክ የምትገኘው የአባካን ከተማ ፍርድ ቤት እህት ማትሪዮና ስፒሪያዲ እና ወንድም አሌክሳንደር ቭዬርጉኖቭ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ሁለቱም የሁለት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት ተበይኖባቸዋል። የሚያሳዝነው ተመሳሳይ ክስ ተመሥርቶባት የነበረችው እህት ኢሪና ሲዶሮቫ ሕይወቷ አልፏል። እርግጥ ማትሪዮና እና አሌክሳንደር አሁን ወህኒ አይወርዱም።
የክሱ ሂደት
መጋቢት 30, 2021
የደህንነት ሠራተኞች የማትሪዮናን እና የአሌክሳንደርን ቤት ፈተሹ
ሐምሌ 17, 2020
ኢሪና ከቀዶ ሕክምና በኋላ ባጋጠማት ችግር ምክንያት ሕይወቷ አለፈ
ግንቦት 20, 2020
ባለሥልጣናት ኢሪና በጽንፈኝነት እንቅስቃሴ ተካፍላለች ብለው ስለጠረጠሩ ምርመራ አደረጉባት
ግንቦት 19, 2020
ባለሥልጣናት አሌክሳንደር በጽንፈኝነት እንቅስቃሴ ተካፍሏል ብለው ስለጠረጠሩ ምርመራ አደረጉበት
ሚያዝያ 20, 2020
በአሌክሳንደር፣ በኢሪና እና በማትሪዮና ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው
አጭር መግለጫ
አምላካችን ይሖዋ ታማኝ አገልጋዮቹን በሙሉ እንደሚመለከታቸውና እንደሚያደንቃቸው እርግጠኞች ነን። እነዚህን ውድ አገልጋዮቹን መንከባከቡን እንደማያቋርጥ ሙሉ እምነት አለን።—ኢሳይያስ 49:15