በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት ታትያና አሉሽኪና ባለቤቷ ቭላዲሚር ከእስር ሲፈታ እቅፍ አድርጋ ስትቀበለው

ሚያዝያ 10, 2020
ሩሲያ

ወንድም ቭላዲሚር አሉሽኪን ከእስር ተፈታ

ወንድም ቭላዲሚር አሉሽኪን ከእስር ተፈታ

ወንድም ቭላዲሚር አሉሽኪን መጋቢት 30, 2020 ከእስር የተፈታ ሲሆን ከሚስቱ ጋር በድጋሚ መገናኘት ችሏል።

ቀደም ሲል እንደተገለጸው ወንድም አሉሽኪን ከእስር ሊፈታ የቻለው የፔንዛ ክልላዊ ፍርድ ቤት መጋቢት 25 ባስተላለፈው ውሳኔ የተነሳ ነው። ፍርድ ቤቱ ያስተላለፈው ውሳኔ በወንድም ቭላዲሚር አሉሽኪን፣ በወንድም ቭላዲሚር ኩልያሶቭ፣ በወንድም አንድሬ ማግሊቭ፣ በወንድም ዴኒስ ቲሞሺን እንዲሁም በእህት ታትያና አሉሽኪና እና በእህት ጋሊያ አልኮቫ ላይ የተላለፈውን ፍርድ የሚቀለብስ ነበር። የፔንዛ ክልላዊ ፍርድ ቤት ጉዳዩ ወደ መጀመሪያው ፍርድ ቤት ተመልሶ በሌላ ዳኛ እንዲታይ ወስኗል። እስከዚያው ግን ስድስቱም የጉዞ ገደብን ጨምሮ በተለያዩ ገደቦች ሥር ይቆያሉ።

ወንድም አሉሽኪን መፈታቱን በመስማታችን ብንደሰትም ይህ ከሆነ ከሁለት ቀናት በኋላ በሰሜን ምሥራቃዊ የሩሲያ ክፍል የሚኖር አንድ ወንድማችን በእምነቱ ምክንያት ተፈርዶበታል። እነዚህ መሠረተ ቢስ ክሶች እስከቀጠሉ ድረስ በሩሲያ የሚኖሩ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በናሆም 1:7 ላይ የሚገኘውን የሚከተለውን ማጽናኛ እንደሚያስታውሱ እንተማመናለን፦ “ይሖዋ ጥሩ ነው፤ በጭንቀትም ቀን መሸሸጊያ ነው። እሱን መጠጊያ ማድረግ የሚፈልጉትን ያውቃል።”