በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ኢጎር ሰሬቭ

ጥር 28, 2021
ሩሲያ

ወንድም ኢጎር ሰሬቭ መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናቱ ምክንያት የአራት ዓመት እስራት ሊፈረድበት ይችላል

ወንድም ኢጎር ሰሬቭ መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናቱ ምክንያት የአራት ዓመት እስራት ሊፈረድበት ይችላል

የፍርድ ውሳኔ የሚሰጥበት ቀን

ሩሲያ ውስጥ በአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል የሚገኘው የቢሮቢድዣን አውራጃ ፍርድ ቤት የወንድም ኢጎር ሰሬቭን ጉዳይ ተመልክቶ ውሳኔ ለመስጠት የካቲት 1, 2021 a ቀጠሮ ይዟል። ወንድም ኢጎር ሰሬቭ አራት ዓመት ሊፈረድበት ይችላል።

አጭር መግለጫ

ኢጎር ሰሬቭ

  • የትውልድ ዘመን፦ 1974 (ቢራካን፣ የአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል)

  • ግለ ታሪክ፦ ሁለት ታናናሽ እህቶች አሉት። ገና ተማሪ እያለ እንጨት በመቁረጥ፣ በአናጺነት እና በኤሌክትሪክ ሥራ ተሠማርቶ ቤተሰቡን ይደግፍ ነበር። ተፈጥሮን ያደንቃል እንዲሁም ዓሣ ማጥመድ ይወዳል

  • በውትድርና አገልግሎት ውስጥ እያለ ስለ ሕይወት ዓላማ ጥያቄ ይፈጠርበት ጀመር። ለጥያቄዎቹ መልስ ለማግኘት ጥረት ያደረገ ሲሆን በኋላ ላይ እሱና አባቱ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ጀመሩ። በ1997 ተጠመቀ። በ1998 ከቪክቶሪያ ጋር ትዳር መሠረተ። ትምህርት የጀመረች ልጅ አለቻቸው

የክሱ ሂደት

ሐምሌ 30, 2019 የሩሲያ ባለሥልጣናት በወንድም ኢጎር ሰሬቭ ላይ የወንጀል ክስ መሠረቱ። ኢጎር የወንጀል ክስ የተመሠረተበት “የይሖዋ ምሥክሮችን ትምህርት ለማስፋፋት” ሲል መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናቱ ነው። የፌዴራል ደህንነት አባላት ሃይማኖታዊ ስብሰባ ሲካሄድ በድብቅ የቀረጹት ቪዲዮ በኢጎር ላይ እንደ ማስረጃ ሆኖ ቀርቧል። አቃቤ ሕጉ የፍርድ ሂደቱ ለሕዝብ ዝግ እንዲሆን ጠይቋል፤ ይህ ያልተለመደ አካሄድ ነው። ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ተቀብሎታል፤ አቃቤ ሕጉ ይህን ጥያቄ ያቀረበው፣ በፍርድ ሂደቱ ላይ የሚገኙ ሰዎች የኢጎርን እምነት እንዳይቀበሉ በሚል ነው።

ኢጎር እንዲህ ብሏል፦ “ፍርድ ቤቱ በቅርቡ የሚያስተላልፈው ውሳኔ ሕይወቴን ሙሉ በሙሉ ይቀይረዋል። ለነገሩ አሁንም ቢሆን ሕይወቴ ተቀይሯል። ከቦታ ቦታ እንዳልንቀሳቀስ እገዳ ተጥሎብኛል። በተጨማሪም የሕግ አካላት ምርመራ እያካሄዱብኝ ያሉት ለምን እንደሆነ ለአሠሪዬ ለማስረዳት ተገድጃለሁ። አለቃዬና የሥራ ባልደረቦቼ የወንጀል ክስ የተመሠረተብኝ ለምን እንደሆነ ለመረዳት ከብዷቸዋል፤ ያም ቢሆን ክርስቲያኖች ከጥንትም ጀምሮ ይሰደዱ እንደነበር ያውቃሉ።”

ለኢጎርና ለቤተሰቡ እንጸልያለን። ይሖዋ ‘በመንፈሱ አማካኝነት ኃይል’ እንደሚሰጣቸው እንተማመናለን።—ኤፌሶን 3:16

a ቀኑ ሊቀየር ይችላል።