ነሐሴ 30, 2019
ሩሲያ
የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም ሞስካሌንኮ ላይ ብይን ሊያስተላልፍ ነው
የካባረቭስክ ክልል የዢለዝናዳሮዥኒይ አውራጃ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት ኢቫን ቢሊኽ፣ በ52 ዓመቱ ወንድም ቫለሪ ሞስካሌንኮ ላይ የሚያስተላልፉት ብይን መስከረም 2, 2019 ይፋ ይሆናል።
ወንድም ሞስካሌንኮ ፌዴራል ደህንነቶችና ፖሊሶች ቤቱን ከበረበሩበት ከነሐሴ 2, 2018 ማለዳ አንስቶ ያለፍርድ እስር ላይ ቆይቷል። ፖሊሶቹ ወንድም ሞስካሌንኮን ያሰሩት ቤቱን ለአምስት ሰዓታት ያህል ከበረበሩ በኋላ ነበር። ወንድም ሞስካሌንኮ ከዓመት በላይ ያለፍርድ ስለታሰረ ልክ እንደ ዴኒስ ክሪስተንሰን ተፈርዶበት ወህኒ ሊወርድ ይችላል የሚል ስጋት አለ።
ታኅሣሥ 18, 2018 ከሳሽ ሞስካሌንኮ እና ተከሳሽ ሩሲያ የሚል አቤቱታ ለአውሮፓ ሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር። እስካሁን ድረስ የሩሲያን ድርጊት በመቃወም ከ50 በላይ አቤቱታዎች ለአውሮፓ ሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ከእነዚህ መካከል የ34ቱ ምላሽ ለሩሲያ መንግሥት ተላልፏል።
በሩሲያ የሚኖሩ ውድ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ‘እየደረሰባቸው ያለውን ስደትና መከራ ሁሉ ችለው በመኖር ባሳዩት ጽናትና እምነት የተነሳ’ እንኮራባቸዋለን። የይሖዋ ድጋፍና በረከት እንዳልተለያቸው በግልጽ ማየት ይቻላል። የፍርድ ቤቱ ብይን ምንም ሆነ ምን ወንድም ሞስካሌንኮ በደስታ ለመጽናት የሚያስፈልገውን ብርታት ይሖዋ እንዲሰጠው እንጸልያለን።—2 ተሰሎንቄ 1:4