በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ኮንስታንቲን ባዤኖቭ

ጥቅምት 28, 2020
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ባዠኖቭ የእስር ጊዜውን ሳይጨርስ እንዲፈታ የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ አደረገ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ባዠኖቭ የእስር ጊዜውን ሳይጨርስ እንዲፈታ የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ አደረገ

ጥቅምት 28, 2020 በዩልያኖቭስክ ክልል የሚገኘው የዲሚትሮግራድ ከተማ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ኮንስታንቲን ባዠኖቭ የእስር ጊዜውን ሳይጨርስ እንዲፈታና ቀሪው የእስር ጊዜ በገንዘብ ቅጣት እንዲቀየርለት የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ አደረገ። ወንድም ባዠኖቭ በአሥር ቀን ውስጥ ይግባኝ መጠየቅ ይችላል።

ወንድም ባዠኖቭ ሰኔ 2018 ያለፍርድ በታሰረበት ወቅት ፍርሃት ተሰምቶት ነበር፤ ይህ መሆኑ አያስገርምም። ይሁንና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በማስታወሻው ላይ መጻፍ ጀመረ። በቃሉ የሚያስታውሳቸውን 500 ገደማ ጥቅሶች መጻፍ ችሏል። በኋላም መጽሐፍ ቅዱስ አገኘ፤ በአራት ወር ውስጥ አንብቦ ጨረሰው። ወንድም ባዠኖቭ ከመጽሐፍ ቅዱስ ያገኛቸውን አበረታች ሐሳቦች ደብዳቤ በመጻፍ ለሌሎች ያካፍል ነበር። በተጨማሪም መንፈሳዊ መዝሙሮችን ይዘምር እንዲሁም አምላክ እንዲረዳው አዘውትሮ ምልጃ ያቀርብ ነበር።

ወንድም ባዠኖቭ ከ340 ቀናት በላይ ያለፍርድ ታስሯል። መስከረም 2019 ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ ሦስት ዓመት ተኩል እስራት ተፈረደበት፤ ያም ቢሆን መንፈሳዊ ልማዱን አላቋረጠም። በይሖዋ እርዳታ እስር ቤት ውስጥ የመታሰቢያውን በዓል ማክበር ችሏል። ወንድም ባዠኖቭ ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ዝምድና መመሥረቱ እየደረሰበት ያለውን ስደት በደስታ እንዲቋቋም ረድቶታል። ስለ ወንድም ባዠኖቭ አሁንም መጸለያችንን እንቀጥላለን።