ግንቦት 23, 2024
ሩሲያ
‘ይሖዋ ከእኔ አይለይም’
በካራቻዬቮ ቺርኬሲያ ሪፑብሊክ የሚገኘው የኡሩፕስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ከወንድም አሌክሴ ፓሲንኮቭ ክስ ጋር በተያያዘ በቅርቡ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍበት የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።
አጭር መግለጫ
የተለያየ መከራ ቢደርስብንም እንኳ ይሖዋ መጠጊያ እንደሚሆነን እና በእሱ ሐሴት ማድረግ እንደምንችል በማወቃችን አመስጋኞች ነን።—መዝሙር 5:11
የክሱ ሂደት
ኅዳር 23, 2021
ባለሥልጣናቱ አሌክሴን በሥራ ቦታው ሳለ በቁጥጥር ሥር አዋሉት፤ ቤቱንም ፈተሹ
ታኅሣሥ 8, 2022
የክስ ፋይል ተከፈተበት
መጋቢት 3, 2023
ቤቱ ለሁለተኛ ጊዜ ተፈተሸ። አሌክሴ እና ዩሊያ ምርመራ ተደረገባቸው
መጋቢት 31, 2023
የአሌክሴ እናት እና ወንድሞች ቤት ተፈተሸ
ጥቅምት 4, 2023
የጉዞ እገዳዎች ተጣሉበት
ታኅሣሥ 14, 2023
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ