ታሪካዊ እመርታዎች በኡዝቤኪስታን
የካቲት 19, 2009—ባለሥልጣናት፣ በታሽኬንት የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች እውቅና እንዲሰጣቸው የቀረበውን 16ኛ ማመልከቻ ውድቅ አደረጉ። ቀደም ሲል በ1997፣ በ1998፣ በ2000፣ በ2001፣ በ2003፣ በ2004፣ በ2005 እና በ2006 የቀረቡ ተመሳሳይ ማመልከቻዎች ተቀባይነት ሳያገኙ ቀርተዋል
ነሐሴ 24, 2006—መንግሥት፣ የፌርጋና የይሖዋ ምሥክሮችን ፈቃድ ሰረዘ
ነሐሴ 1999—መንግሥት፣ በቺርቺክ እና በፌርጋና የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮችን በድጋሚ መዘገበ
ግንቦት 1, 1998—መንግሥት፣ ሃይማኖቶች በድጋሚ እንዲመዘገቡ የሚጠይቅ የሃይማኖቶች መተዳደሪያ ደንብ ሥራ ላይ እንዲውል አደረገ
ታኅሣሥ 1996—የይሖዋ ምሥክሮች በታሽኬንት እውቅና ለማግኘት ያቀረቡትን የመጀመሪያ ማመልከቻ መንግሥት ሳይቀበለው ቀረ
ታኅሣሥ 17, 1994—መንግሥት፣ በቺርቺክ እና በፌርጋና ለሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ሕጋዊ እውቅና ሰጠ
ታኅሣሥ 8, 1992—አዲሱ መንግሥት ለመሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች ዋስትና የሚሰጥ ሕገ መንግሥት አጸደቀ
መስከረም 1, 1991—ኡዝቤኪስታን ነፃ አገር ሆነች
1960ዎቹ—አንግሬን እና ቺርቺክ ውስጥ የይሖዋ ምሥክሮች እንቅስቃሴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሪፖርት ተደረገ