መስከረም 4, 2023
ዓለም አቀፋዊ ዜና
በፍርሃት ከመራድ ይልቅ በእምነት መበርታት
በሴቫስቶፖል፣ ክራይሚያ የሚገኘው የጋጋሪንስኪ ክልል ፍርድ ቤት በቅርቡ በወንድም ቪክቶር ኩዲኖቭ እና በወንድም ሰርጌ ዢጋሎቭ ላይ ብይን እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍ የሚፈልገውን ፍርድ ገና አላሳወቀም።
አጭር መግለጫ
“[በአገልጋዮቹ] ሰላም የሚደሰተው ይሖዋ” ላሳዩት ትዕግሥትና ጽናት ቪክቶርንና ሰርጌን መባረኩን እንደሚቀጥል እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 35:27
የክሱ ሂደት
ነሐሴ 24, 2022
የክስ ፋይል ተከፈተባቸው። ቤቶቻቸው ተፈተሹ። ተይዘው ወደ ማረፊያ ቤት ተወሰዱ
ነሐሴ 26, 2022
ከማረፊያ ቤት ወጥተው በቁም እስር እንዲቆዩ ተደረገ
ጥቅምት 17, 2022
ከቁም እስር ተለቀቁ፤ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጣለባቸው
ሚያዝያ 13, 2023
ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ