በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መጽሐፍ ቅዱስ ሳይጋቡ አብሮ መኖርን በተመለከተ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ሳይጋቡ አብሮ መኖርን በተመለከተ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 አምላክ የሰው ልጆች ‘ከፆታ ብልግና እንዲርቁ’ እንደሚፈልግ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (1 ተሰሎንቄ 4:3) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው “የፆታ ብልግና” የሚለው ቃል ምንዝርን፣ ግብረ ሰዶምንና ባልተጋቡ ሰዎች መካከል የሚፈጸምን የፆታ ግንኙነት ይጨምራል።

 አምላክ ሰዎች ጋብቻ የመመሥረታቸው ጉዳይ የሚያሳስበው ለምንድን ነው?

  •   የጋብቻ ዝግጅትን የመሠረተው አምላክ ነው። አምላክ አዳምንና ሔዋንን በትዳር በማጣመር የጋብቻ ዝግጅትን አቋቁሟል። (ዘፍጥረት 2:22-24) የአምላክ ዓላማ አንድ ወንድና አንዲት ሴት የጋብቻ መሐላ ሳይፈጽሙ አብረው እንዲኖሩ አልነበረም።

  •   ለሰው ልጆች የሚጠቅመውን የሚያውቀው አምላክ ነው። አምላክ ጋብቻን ያቋቋመው በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚመሠረት ዘላቂ ጥምረት እንዲሆን አድርጎ ሲሆን ጋብቻ ለሁሉም የቤተሰብ አባላት ደስታና ጥበቃ የሚያስገኝ እንዲሆን ይፈልጋል። አንድ ቀላል ምሳሌ እንመልከት። የቤት ዕቃ የሚያመርት ድርጅት የሚሰጠው መመሪያ ዕቃውን በትክክል ለመገጣጠም እንደሚረዳ ሁሉ አምላክ የሚሰጠው መመሪያም አስደሳች የቤተሰብ ሕይወት ለመመሥረት ይረዳል። የአምላክን መሥፈርቶች የሚከተሉ ሰዎች ምንጊዜም ጥቅም ያገኛሉ።—ኢሳይያስ 48:17, 18

    የቤት ዕቃ የሚያመርት ድርጅት የሚሰጠው መመሪያ ዕቃውን በትክክል ለመገጣጠም ይረዳል። አምላክ የሚሰጠው መመሪያም አስደሳች የቤተሰብ ሕይወት ለመመሥረት ይረዳል

  •   ከጋብቻ ውጭ የሚፈጸም የፆታ ግንኙነት ከባድ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል። ለምሳሌ ላልተፈለገ እርግዝና፣ ለአባላዘር በሽታዎችና ለስሜት ቀውስ ሊዳርግ ይችላል።

  •   ሰዎች በፆታ ግንኙነት አማካኝነት ልጅ የመውለድ ችሎታ እንዲኖራቸው ያደረገው አምላክ ነው። አምላክ ሕይወትን ቅዱስ አድርጎ ይመለከተዋል፤ ዘር የመተካት ችሎታም ልዩ ስጦታ ነው። ለዚህ ስጦታ አክብሮት እንዳለን ማሳየት የምንችለው አምላክ ያቋቋመውን የጋብቻ ዝግጅት በማክበር ነው፤ አምላክም እንዲህ እንድናደርግ ይፈልጋል።—ዕብራውያን 13:4

 በደንብ እንደሚጣጣሙ ለማረጋገጥ ከጋብቻ በፊት አብሮ መኖር ምን ችግር አለው?

 ስኬታማ ትዳር መመሥረት የሚቻለው ከጋብቻ በፊት ያለምንም ቃል ኪዳን “ለሙከራ ያህል” አብሮ በመኖር አይደለም። ከዚህ ይልቅ ጥሩ ትዳር መመሥረት የሚቻለው ሁለቱም ምንም ነገር ቢያጋጥም አብረው ለመኖር ቁርጠኛ ከሆኑና ችግሮችን ለመፍታት ተባብረው የሚሠሩ ከሆነ ነው። a በጋብቻ መተሳሰራቸው አብረው ለመኖር ያላቸውን ቁርጠኝነት ያጠናክረዋል።—ማቴዎስ 19:6

 ባለትዳሮች ትዳራቸውን ማጠናከር የሚችሉት እንዴት ነው?

 ፍጹም የሆነ ትዳር የለም። ሆኖም ባለትዳሮች የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር በተግባር የሚያውሉ ከሆነ አስደሳች የትዳር ሕይወት ሊኖራቸው ይችላል። ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ የሚከተሉትን ምክሮች ይሰጣል፦

aስኬታማ ቤተሰቦች—ቃል ኪዳንን ማክበር” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።