የይሖዋ ምሥክሮች ፆታዊ ጥቃትን በተመለከተ ወላጆችንም ሆነ ልጆችን ያስተምራሉ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲወዷቸው፣ እንዲያስተምሯቸውና ከአደጋ እንዲጠብቋቸው እንዲሁም የአምላክ ስጦታ እንደሆኑ አድርገው እንዲመለከቷቸው ይመክራል። (መዝሙር 127:3፤ ምሳሌ 1:8፤ ኤፌሶን 6:1-4) ወላጆች ልጆቻቸውን ከተለያዩ አደገኛ ሁኔታዎች ሊጠብቋቸው ይገባል፤ ከእነዚህም አንዱ ፆታዊ ጥቃት ነው።
ላለፉት በርካታ አሥርተ ዓመታት የይሖዋ ምሥክሮች፣ ቤተሰቦች እርስ በርሳቸው ጤናማ ግንኙነት እንዲኖራቸው የሚያበረታቱ ጽሑፎችንና ሌሎች መረጃዎችን አዘጋጅተው ሲያሰራጩ ቆይተዋል። በተጨማሪም ልጆችን ከፆታ ጥቃት ለመጠበቅ እንዲሁም ፆታዊ ጥቃት የሚፈጽሙ ሰዎችን በተመለከተ ለልጆች ትምህርት ለመስጠት የሚረዱ ጽሑፎችን ለወላጆች አዘጋጅተዋል። የይሖዋ ምሥክሮች ይህን ጉዳይ በተመለከተ ግልጽ የሆነ መመሪያ ሲሰጡ እንደቆዩ የሚያሳዩ አንዳንድ ርዕሶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል። እነዚህ ርዕሶች በምን ያህል ቋንቋዎች እንደተዘጋጁና ምን ያህል ቅጂዎች እንደተሰራጩ ልብ ለማለት ሞክር። a
-
ጽሑፍ፦ የካቲት 8, 1981 ንቁ! መጽሔት እትም (እንግሊዝኛ)
የቅጂው ብዛት፦ 7,800,000
የቋንቋው ብዛት፦ 34
ርዕስ፦ Help for the Victims of Incest
ጽሑፍ፦ የጥቅምት 1, 1983 መጠበቂያ ግንብ እትም (እንግሊዝኛ)
የቅጂው ብዛት፦ 10,050,000
የቋንቋው ብዛት፦ 102
ርዕስ፦ Child Molesting—Every Mother’s Nightmare; Child Molesting—‘Who Would Do a Thing Like That?’; Child Molesting—You Can Protect Your Child
ጽሑፍ፦ የጥር 22, 1985 ንቁ! መጽሔት እትም (እንግሊዝኛ)
የቅጂው ብዛት፦ 9,800,000
የቋንቋው ብዛት፦ 54
ርዕስ፦ The Innocent Victims of Child Abuse; The Secret Wounds of Child Abuse
ጽሑፍ፦ የጥቅምት 8, 1991 ንቁ! መጽሔት እትም (እንግሊዝኛ)
የቅጂው ብዛት፦ 12,980,000
የቋንቋው ብዛት፦ 64
ርዕስ፦ Your Child Is in Danger!; How Can We Protect Our Children?; Prevention in the Home
ጽሑፍ፦ የጥቅምት 8, 1993 ንቁ! መጽሔት እትም
የቅጂው ብዛት፦ 13,240,000
የቋንቋው ብዛት፦ 67
ርዕስ፦ ልጆቻችሁን ጠብቁ
ጽሑፍ፦ Public Service Announcement Video Number 4, በ2002 የተዘጋጀ
የቋንቋው ብዛት፦ 2
ርዕስ፦ ኢየሱስ ጥበቃ ያገኘው እንዴት ነው?
ጽሑፍ፦ ከታላቁ አስተማሪ ተማር የተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 32፣ በ2003 የታተመ
የቅጂው ብዛት፦ 39,746,022
የቋንቋው ብዛት፦ 141
ርዕስ፦ እያንዳንዱን ወላጅ የሚያሳስብ አደጋ፤ ልጆቻችሁን ከጥቃት መጠበቅ የምትችሉት እንዴት ነው?፤ ቤታችሁ አስተማማኝ የእረፍት ቦታ እንዲሆን አድርጉ
ጽሑፍ፦ የጥቅምት 2007 ንቁ! መጽሔት
የቅጂው ብዛት፦ 34,267,000
የቋንቋው ብዛት፦ 81
ርዕስ፦ ፆታዊ ጥቃት እንዳይደርስብኝ ራሴን መጠበቅ የምችለው እንዴት ነው?፤ ወላጆች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች፦ ከልጄ ጋር ስለ ፆታ ጉዳዮች ማውራት ይኖርብኛል?
ጽሑፍ፦ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 1፣ ምዕራፍ 32 እና ተጨማሪ ክፍል፣ በ2011 የታተመ
የቅጂው ብዛት፦ 18,381,635
የቋንቋው ብዛት፦ 65
ርዕስ፦ ወላጆች ልጆቻቸውን ስለ ፆታ ማስተማር የሚችሉት እንዴት ነው?
ጽሑፍ፦ jw.org ድረ ገጽ፤ መስከረም 5, 2013 የወጣ ርዕስ
የቋንቋው ብዛት፦ 64
የይሖዋ ምሥክሮች ፆታዊ ጥቃት የሚፈጽሙ ሰዎች ከሚያደርሱት ጉዳት ልጆችን ለመጠበቅ ለወላጆችም ሆነ ለልጆች ትምህርት መስጠታቸውን ይቀጥላሉ።
a የሕትመቱ ቀን የተጻፈው ከእንግሊዝኛው እትም አንጻር ነው።