በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

‘ምሥራቹን ስበኩ!’

የ2024 የይሖዋ ምሥክሮች የክልል ስብሰባ

መግቢያ በነፃ ነው ሙዳየ ምጽዋት አይዞርም

የስብሰባው ጎላ ያሉ ገጽታዎች

የዓርብ ፕሮግራም፦ በወንጌሎች ውስጥ የሚገኘው ስለ ኢየሱስ የሚገልጸው ምሥራች፣ የኢየሱስን ሕይወት በትክክል እንደሚዘግብ እርግጠኛ እንድንሆን የሚያደርጉን ምክንያቶች ይብራራሉ። በተጨማሪም በዛሬው ጊዜ ከእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ምን ጥቅም እንደምናገኝ እንማራለን።

የቅዳሜ ፕሮግራም፦ ኢየሱስ ከሚወለድበት ሁኔታና ከልጅነት ሕይወቱ ጋር በተያያዘ የትኞቹ ትንቢቶች ተነግረዋል? እነዚህ ትንቢቶች በእርግጥ ተፈጽመዋል?

የእሁድ ፕሮግራም፦ “መጥፎ ዜና የማያሸብረን ለምንድን ነው?” የሚል ርዕስ ባለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ንግግር ላይ የዓለም ሁኔታ እየተባባሰ ቢሆንም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የወደፊቱን ጊዜ በልበ ሙሉነት የሚጠባበቁት ለምን እንደሆነ ይብራራል።

ድራማ

የኢየሱስ ወንጌል፦ ክፍል 1

እውነተኛው የዓለም ብርሃን

ኢየሱስ የተወለደበት ተአምራዊ የሆነ መንገድ፣ ከልጅነት ሕይወቱ ጋር ከተያያዙ በርካታ ትኩረት የሚስቡ ክንውኖች መካከል አንዱና የመጀመሪያው ብቻ ነው። ኢየሱስ ሕፃን ሳለ አንድ ንጉሥ ሊገድለው ይፈልግ ስለነበር ወላጆቹ ሕይወቱን ለማትረፍ ሲሉ ወደ ግብፅ ወስደውታል። ከፍ ካለ በኋላ፣ በዘመኑ የነበሩትን ታላላቅ አስተማሪዎች አስደምሟል። ዓርብ እና ቅዳሜ በሚቀርቡት የድራማው ሁለት ክፍሎች ላይ እነዚህና ሌሎች ትዕይንቶች ይታያሉ።

ስለ ዘንድሮው ስብሰባ የሚገልጹትን የሚከተሉትን ቪዲዮዎች ይመልከቱ

የክልል ስብሰባዎቻችን ምን ይመስላሉ?

ይህ ቪዲዮ የይሖዋ ምሥክሮች የክልል ስብሰባዎች ምን እንደሚመስሉ ያሳያል።

የ2024 የይሖዋ ምሥክሮች የክልል ስብሰባ፦ ‘ምሥራቹን ስበኩ!’

በዚህ ዓመት የክልል ስብሰባ ላይ ምን እንደምንማር ይመልከቱ።

የድራማ ማስተዋወቂያ፦ የኢየሱስ ወንጌል

ብዙዎች ኢየሱስ ስለተወለደበት ተአምራዊ ሁኔታ ያውቃሉ። ሆኖም ከዚያ አስደናቂ ክንውን በፊትም ሆነ በኋላ ምን ነገሮች ተከናውነዋል?